Homeዜናና ወቅታዊዜናኢንዶኔዥያ የሐላል ኢንዱስትሪን ለማሳደግ ብሔራዊ እስላማዊ የፋይናንስ ማዕከል አቋቋመች

ኢንዶኔዥያ የሐላል ኢንዱስትሪን ለማሳደግ ብሔራዊ እስላማዊ የፋይናንስ ማዕከል አቋቋመች

በደቡብ ምሥራቅ እስያ ውስጥ የምትገኘው ኢንዶኔዥያ፤ የሐላል ኢንዱስትሪን ለማሳደግ ብሔራዊ እስላማዊ የፋይናንስ ማዕከል ማቋቋሟን አስታወቀች፡፡ የማዕከሉን መከፈት ይፋ ያደረጉት የኤንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት ሀገራቸው በሐላል ኢንዱስትሪ ቀዳሚ የመሆን ሰፊ ዕድል እንዳላት ተናግረዋል፡፡

የኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ የእስላማዊ የፋይናንስ ማዕከሉን መከፈት ያበሰሩት ትናንት ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ነው፡፡ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ማዕከሉን መክፈት ያስፈለገው ሸሪዓዊ መር ኢኮኖሚን ለማሳደግ እንዲሁም የሃገር ውስጥ የሐላል ኢንዱስትሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ በማለም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ሀገራቸው ኢንዶኔዥያ የሀገር ውስጥ የሐላል ኢንዱስትሪውን ማሳደግ ከቻለች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆን እድሏ ሰፊ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ጆኮ ዊዶዶ የሚመሯት ኢንዶኔዥያ፤ ከአጠቃላይ ሕዝቧ መካከል 87 በመቶው ሙስሊም ነው፡፡ ይህንኑ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ በተለይ በኢንዶኔዥያ ውጥ ከወለድ ነጻ ባንኮች የማሳደግ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተው ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ ጆኮ ዊዶዶ ኢንዶኔዥያ ከወለድ ነጻ ባንኮችን በማሳደግ፤ በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ባንኮች የጥራት ደረጃ መመዘኛ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ ኢንዶኔዥያ ይህን ማሳካት የምትችል ከሆነ የዓለም አቀፍ የሐላል ኢንዱስተሪ ዋንኛዋ መዳረሻ የመሆን እድሏ እያደገ እንደሚሄድም ተናግረዋል፡፡

የኢንዶኔዥያ እስላማዊ የፋይናንስ ማእከል በሚል ሥያሜ የማዕከሉን መከፈት ይፋ ያደረገችው ኢንዶኔዥያ፤ ትልቁ እስላማዊ ባንክ ባንክ ሸሪዓ ኢንዶኔዥያ እንዲሁም በመንግሥት የሚተዳደረው ዳናሬስካ ሆልዲንግ ኩባንያም በዚህ ማእቀፍ ስር እንደሚታቀፉ አስታውቃለች፡፡

ኢንዶኔዥያ የሀገራትን እስላማዊ ኢኮኖሚ ጥንካሬ የሚመዝነው የእስላማዊ ኢኮኖሚ መለኪያ፤ እ.አ.አ በ2023 ባወጣው መረጃ መሠረት በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡ በመለኪያው በቀዳሚነት የተቀመጠችው ሌላኛዋ የደቡብ ምሥራቅ ሀገር ማሌዥያ ስትሆን፣ ቀጣዩን ደረጃ ሳዑዲ ዐረቢያ ይዛለች፡፡

እስላማዊ ፋይናንስ ከሰባቱ የሐላል ኢንስዱስትሪ ዘርፎች ውስጥ የሚታቀፍ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሐላል ኢንዱስትሪ በሥሩ ሐላል ፋይናንስን ጨምሮ ምግብ፣ ሐላል ቱሪዝም፣ ሐላል ፋሽን፣ ሐላል ሚዲያ እና መዝናኛ፣ የመድኃኒት እና ሐላል መዋቢያዎችን የሚያካትት ነው።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular