Homeዜናና ወቅታዊዜናእስራኤል አፍሪካውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን የመኖሪያ ፍቃድ እሰጣለሁ በሚል ለጋዛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንደምትመለምላቸው...

እስራኤል አፍሪካውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን የመኖሪያ ፍቃድ እሰጣለሁ በሚል ለጋዛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንደምትመለምላቸው ተጋለጠ

እስራኤል አፍሪካውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን የመኖሪያ ፍቃድ እሰጣለሁ በሚል ሰበብ ለጋዛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንደምትመለምላቸው ያጋለጠው ሃአሬትዝ የተሰኘው ጋዜጣ ነው፡፡ የእስራኤል ባለሥልጣናት ድርጊቱን የሚፈጽሙት በመከላከያ እንዲሁም የሕግ ተቋማት ድጋፍ በተቀናጀ መንገድ መሆኑንም ጋዜጣው አስነብቧል፡፡

በምልመላው ሒደት ውስጥ ያለፉ አፍሪካዊያን ጥገኝኘት ጠያቂዎች፤ የእስራኤል ባለሥልጣናት የመኖሪያ ፍቃድ ታገኛላችሁ በሚል በጋዛ ለሚያካሔዱት “አደገኛ” የሚባል ኦፕሬሽን ቢመለመሉም ቀድሞ የተገባላቸው ቃል ተፈጻሚ እንዳልሆነ ገልጸዋል ተብሏል፡፡

በዘገባው ሥሙ ያልተጠቀሰ ለወታደራዊ ኦፕሬሽኑ የተመለመለ አፍረካዊ ጥገኝነት ጠያቂ፤ በጋዛ ኦፕሬሽን ላይ ለመሳተፍ የሁለት ሳምንት ሥልጠና ከወሰደ በኋላ የሰነዶቹን ቅጂ እንዲልክ በአንድ ባለሥልጣን ተነግሮት የተባለውን ቢፈጽምም፤ የተገባለት ቃል እንዳልተፈጸመ አጋልጧል፡፡

ጋዜጣው ከተመልማዮቹ መካከል ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ለማረጋገጥ ባደረግኩት ጥረት አንድም ሰው አላገኘሁም ብሏል፡፡ በተጨማሪም ጥገኝነት ጠያቂዎች ከጋዛ ውጪ ሌሎች ኦፕሬሽኖች ላይ እንዲሳተፉ እንደሚገደዱ ተገልጿል፡፡

በእስራኤል 30 ሺሕ ገደማ ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ለማግኘት የሚጠባበቁ አፍሪካያዊያን እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ጥገኝነት ጠያቂዎቹ ፀረ ስደተኝነት አቋም በሚያንጸባርቁ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤንያሚን ኔታንያሁ ባሉ ፖለቲከኞች አስተያየትበከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደመኖሩ ይነገራል፡፡ ከጥገኝነት ጠያቂዎች ውስጥ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ይገኙበታል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular