Homeዜናና ወቅታዊዜናፍልስጤምን የሚደግፉ ዐስር ሺሕዎች የተሳፉበት ሠልፍ በለንደን ተካሔደ

ፍልስጤምን የሚደግፉ ዐስር ሺሕዎች የተሳፉበት ሠልፍ በለንደን ተካሔደ

ፍልስጤምን የሚደግፉ ዐስር ሺሕዎች የተሳፉበት ሠልፍ በለንደን የተካሔደው በዛሬው እለት ነው። ሠልፈኞቹ ዩናይትድ ኪንግደም ለእስራኤል የምትሰጠውን የጦር መሣሪያ ሙሉ ለሙሉ እንድታቆም ጠይቀዋል።

ዛሬ ቅዳሜ በእንግሊዝ ለንደን ከተማ የተካሔደው የተቃውሞ ሠልፍ፣ በጀመረበት ሬጀንት ጎዳና የሠልፉ አስተባባሪዎች ፍልስጤምን የሚደግፉና እስራኤልን የሚነቅፉ ንግግር ያሰሙበት ነበር። የፍልስጤምን ሰንደቅ አላማ የሚያውለበልቡ በርካቶች በታደሙት ሠልፍ ላይ፣ ብሪታንያ እስራኤልን በጦር ማስታጠቋን ሙሉ ለሙሉ እንድታቆም የሚጠይቁ ጥሪዎች ተስተጋብተዋል።

በለንደን የተካሔደው የተቃውሞ ሠልፍ የተከናወነው፣ ዩናይትድ ኪንግደም ለእስራኤል የምትሸጣቸው አንዳንድ የጦር መሣሪያዎች ዓለም አቀፍ ሕግ የሚጥስ ተግባር ሊፈፅምባቸው ስለሚችል በሚል ሽያጯን መግታቷን ካሳወቀች በኋላ ነው።

የዩናይትድ ኪንግደም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ በተያዘው ሳምንት ሀገራቸው ወደ እስራኤል ከምትልካቸው 350 የጦር መሣሪያዎች መካከል 30 የሚሆኑትን አግዳለች ብለዋል። ወደ እስራኤል እንዳይላኩ ከታገዱት የጦር መሣሪያዎች መካከል የጦር አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች እና ድሮኖች ይገኙበታል።

በዛሬው እለት በለንደን ፍልስጤምን በመደገፍ የተካሔደው ሠልፍ፣ እስራኤል በጋዛ በመስከረም ወር የጀመረችውን ጥቃት ተከትሎ የተከናወነ 18ኛ ሠልፍ ነው። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular