የሳዑዲ ዐረቢያ እስላማዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኪርጊዝታን እስላማዊ ጉዳዮች አስተዳደር ጋር በመተባበር ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የቁርኣን ውድድር አስጀመሩ፡፡ በኪርጊዝታን ሰባት ግዛቶች እና ሁለት ከተሞች ውስጥ የተካሄደው የቁርኣን ውድድር፤ በሀገሪቱ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በውድድሩ መክፈቻ ላይ 270 ሴቶች በማጣሪያው ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ተሳታፊዎች በዚህ ውድድር ላይ በአራት ምድብ የሚሳተፉ ሲሆን፣ በዐስር እና ሐያ ጁዝ የቁርኣን ሒፍዝ እንዲሁም በተጅዊድ ተወዳድረዋል፡፡
የውድድሩ አዘጋጆች ቀዳሚውን ማጣሪያ በማካሄድ፤ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ወደ ፍጻሜው የሚያልፉ ተሳታፊዎች የሚለዩበት ውድድር እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡ የውድድሩ ፍጻሜ በማግሥቱ ረቡዕ በቢሽኬክ በሚገኘው ኢማም ሳራክሲ መስጂድ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ በዚህ የፍጻሜ ውድድር ላይ የሳዑዲ አረቢያ እና ኪርጊዝታን የእስልምና ሊቃውንት ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ኪርኪዝታን ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ከሳዑዲ ዐረቢያ ጋር በመተባበር ወንዶችን ብቻ ያሳተፈ የቁርኣን ውድድር አዘጋጅታ ነበር፡፡












