እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎችን የፍቃድ አሰጣጥ ሒደት ማጠናቀቁን ገለጸ

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎችን የፍቃድ አሰጣጥ ሒደት ማጠናቀቁን ገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎችን የፍቃድ አሰጣጥ ሒደት ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡ የባንኩ ኃላፊዎች ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት ከተካሔደ በኋላ አመልካቾች ፍቃድ ያገኛሉ ብለዋል፡፡

ባንኩ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎችን የፍቃድ አሰጣጥ ሒደት ማጠናቀቁን የገለጸው፤ ኢትዮጵያ አዲስ በሥራ ላይ ባዋለችው የውጭ ምንዛሬ መመርያ መሠረት የግል ውጭ ምንዛሬ ቢሮ ለመክፈት የሚፈልጉ የሥራ ፍቃድ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ በማቅረብ አመልካቾችን ከተቀበለ በኋላ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሥራ ላይ በዋለው አዲስ የውጭ ምንዛሬ መመርያ መሠረት የግል ውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት የሚፈልጉ የሥራ ፍቃድ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ ያቀረበው ነሐሴ 2/2016 ነበር፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ቁጥጥር እና የመጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አበባየሁ ዱፌራ፤ የውጭ ምንዛሬ ቢሮ በግል ለመክፈት ፍላጎት ያሳዩ አካላትን ባንኩ በደስታ እንደተቀበለ በመግለጽ፣ ከንግድ ሚኒስቴር ጋር ውይይት ከተካሔደ በኋላ ፍቃድ መስጠት እንደሚጀመር ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው ወደሚወሰንበት የገበያ ሥርዐት መሸጋገሩን ባለፈው ሐምሌ ወር መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንኑ የገበያ ሥርዐት ተከትሎ ይፋ የተደረገው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ፤ በባንክ ስር ያልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሬ መገበያያዎች እንዲቋቋሙ እንደሚፈቀድ ይገልጻል፡፡ እነዚህ መገበያያዎች የውጭ ምንዛሬ ጥሬ ገንዘብ በገበያ ዋጋ እንዲገዙ እና እንዲሸጡ የሥራ ፍቃድ ይሰጣቸዋል ተብሏል። 

ብሔራዊ ባንክ በገበያ ላይ ተመሥርተው የውጭ ምንዛሬ በጥሬ ገንዘብ መግዛት እና መሸጥ የሚፈልጉ የውጭ የግል ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲቋቋሙ በፈቀደው መሠረት ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የሌላ ሀገር ዜግነት ላላቸው ኢትዮጵያዊያን ነበር፡፡ የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘብ በመግዛት እና መሸጥ ላይ ብቻ እንዲሰማሩ የተፈቀደላቸው እነዚህ የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች፤ በሌላ የባንክ ሥራ ላይ መሠማራት አይችሉም፡፡

የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮ ለመክፈት ፍቃድ የሚጠይቅ አካል 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል ሊኖረው እንደሚገባ ሲገለጽ፤ ከዚህ በተጨማሪም 30 ሚሊዮን ብር የዋስትና ተቀማጭ ገንዘብ በዝግ አካውንት ውስጥ በማንኛውም ባንክ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡ የግል ውጭ ምንዛሬ ቢሮው ለሁለት ዓመታት ያህል በሥራ ላይ ከቆየ በኋላ የዋስትና ተቀማጭ ገንዘቡ ይለቀቀቅለታል፡፡

ብሔራዊ ባንክ የቢሮዎቹ መቋቋም የግል ውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች መቋቋም የውጭ ምንዛሬ ገበያን መሠረት ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት የሚሹ ደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያግዝ መሆኑን ቀደም ብሎ ገልጿል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular