እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናምክር ቤቱ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ ሊያዘጋጅ መሆኑን ገለጸ

ምክር ቤቱ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ ሊያዘጋጅ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመጪው ምርጫ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ መመሪያ ሊያዘጋጅ መሆኑን ገለጸ። ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የዑለማ ምክር ቤት እና ለአማካሪዎች በጻፉት ደብዳቤ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አጭር ጥናታዊ ጽሑፍ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል።

ምክር ቤቱ ለመጪው ምርጫ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ መመሪያ ሊያዘጋጅ መሆኑን የገለጸው ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 27/2016 ነው። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሸሪዐን መሠረት ያደረገ የምርጫ መመሪያ ሊያዘጋጅ መሆኑን የገለጸው፣ በፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ኢብራሂም በኩል በቀጣዩ ዓመት ምርጫ እንደሚያካሄድ ማረጋገጫ ከሰጠ በኋላ ነው።

ሸይኽ ኢብራሂም ከሁለት ቀን በፊት በተሰጠ የምክር ቤቱ መግለጫ ወቅት፣ በቀጣይ የሚከናወነው የምክር ቤቱ ምርጫ ሒደት ሸሪዐን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ጥቆማ ሰጠተው ነበር። ፕሬዝዳንቱ በዚህ ንግግራቸው “ፖለቲካዊ አይደለም” ያሉትን ምርጫ፣ “ከመረጣችሁኝ ይህን እሠራለሁ፣ ምረጡኝ ተብሎ ለሥልጣን የሚፎካከሩበት” አለመሆኑንም ገልጸው ነበር። ምርጫው በሰላማዊ እና ኃላፊነት በተሞላበት መንፈሥ እንዲካሄድም በመግለጫው አሳስበዋል።

ይህንኑ ተከትሎም ፕሬዝዳንቱ የዑለማ ምክር ቤት እና አማካሪ ቦርድ ለዚህ የሚያግዝ ጥናታዊ ጽሑፍ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተገልጿል።

ምርጫውን በቀጣዩ ዓመት አከናውናለሁ ያለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤ አመራሮች፣ ኃላፊነት ላይ ከወጡ ባለፈው ሐምሌ ወር ሁለት ዓመት ደፍኗል። የምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ አባላት በ2014 ኃላፊነት ላይ ሲወጡ የተቀመጠላቸው የሥልጣን ዕድሜ ሦስት ዓመት እንደነበር የሚታወስ ነው።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular