እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናየሙጅመዕ አት ተቅዋ መድረሳ የክረምት ሥልጠና መዝጊያ መርሐ ግብር አከናወነ

የሙጅመዕ አት ተቅዋ መድረሳ የክረምት ሥልጠና መዝጊያ መርሐ ግብር አከናወነ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የሙጅመዕ አት ተቅዋ መድረሳ የክረምት ሥልጠና መመዝጊያ መርሐ ግብር በዛሬው እለት አከናወነ። መድረሳው በተመላላሽ እና በአዳሪ መርከዝ በድምሩ 260  ተማሪዎችን ማሠልጠኑን አሳውቋል።

ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 27/2016 በተከናወነው የሙጅሙዕ አት ተቅዋ መድረሳ የሥልጠና መዝጊያ መርሐ ግብር ላይ፣ በተመላላሽ 223 እና በአዳሪ መርከዝ 37 በድምሩ 260 ተማሪዎች ሥልጠና ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ለሁለት ወር በተከናወነው የሥልጠና መርሐ ግብር ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች በተመላላሽ በጀማሪ ደረጃ ቃኢዳ ኑራኒያ ተምረው አጠናቀዋል ተብሏል። በዚህ ፕሮግራም 88 ተማሪዎች ለሥልጠና ተመዝግበው 23 ተማሪዎች ተምረው ማጠናቀቃቸው በመርሐ ግብሩ መዝጊያ ላይ ኃላፊዎቹ ገልፀዋል።

በሁለተኛው ፕሮግራም የነዘር (ቲላዋ) ክፍል 123 ተማሪዎች ተሳታፊ ሲሆኑ፣ በሦስተኛው የሂፍዝ ፕሮግራም 16 ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ተማሪዎች በሁለት ወር ቆይታቸው ከቁርኣን ትምህርታቸው ጎን ለጎን የአቂዳ፣ ሐዲሥ፣ ፊቂህ፣ ሲራ፣ ኸጥ እንዲሁም የተርቢያ ትምህርት ማግኘታቸውን የመድረሳው ኃላፊዎች በመርሐ ግብሩ መዝጊያ ተናግረዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular