እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናስዊድን ቁርኣን ያቃጠሉ ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ መሠረተች

ስዊድን ቁርኣን ያቃጠሉ ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ መሠረተች

የስዊድን መንግሥት ዐቃቤ ሕግ፤ ባለፈው ዓመት ቁርኣን ያቃጠሉ ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ መመሥረቱ ታወቀ፡፡ የግለሰቦቹ ክስ “አንድን ማንነት ወይም ቡድን ማንኳሰስ” የሚል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ግለሰቦቹ ባለፈው ዓመት በተለያዩ አራት አጋጣሚዎች የቁርኣንን እንዲሁም የእስልምና ክብር የሚያንኳስሱ ድርጊቶችን መፈጸማቸውን ያስታወቀ ሲሆን፣ በዚሁ ጊዜ ጸያፍ ቃላትን ሲጠቀሙ እንደነበርም ገልጿል፡፡

ፖሊስ በዚህ ሳምንት ሥማቸውን ይፋ ያደረጋቸው ሁለቱ ግለሰቦች፤ ባለፈው ዓመት የፈጸሙት ድርጊት ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር፡፡ በወቅቱ በሀገሪቱ የሚገኙ የእስልምና ሊቃውንት ድርጊቱን በመኮነን የስዊድን መንግሥት ተመሳሳይ ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል የሕግ ማዕቀፍ ጠበቅ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ስዊድን በተለይ ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተው ይነገራል፡፡

የስዊድን ዐቃቤ ሕግ ክስ የእስልምና ክብር በመዳፈራቸው ክስ በመሠረታቸው ሁለት ግለሰቦች ላይ ማሥረጃ አድርጎ ያቀረበው፤ ድርጊቱ በሚፈጸምበት ወቅት የተቀረጹ ቪድዮዎችን ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular