Homeዜናና ወቅታዊዜናየግብጹ አል አዝሃር ዩኒቨርሲቲ የቁርኣን ጥናት ቀን ሊያከብር ነው

የግብጹ አል አዝሃር ዩኒቨርሲቲ የቁርኣን ጥናት ቀን ሊያከብር ነው

አንጋፋው የግብጹ ትምህርት ተቋም አል አዝሃር ዩኒቨርሲቲ፤ የቁርኣን ጥናት ቀን ሊያከብር መሆኑን ይፋ አደረገ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ይፋ ባደረገው የቁርኣን ቀን ከግብጽ የተለያዩ ግዛቶች የሚሰባሰቡ ከ6 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

አንጋፋው የግብጹ ትምህርት ተቋም አል አዝሃር ዩኒቨርሲቲ፤ የቁርኣን ጥናት ቀን የሚያከብረው ነገ ቅዳሜ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የቁርኣን ጥናት ቀን በሚል የሰየመው መሰናዶ ያዘጋጀው፤ ተማሪዎች ከቄርኣን ጋር የሚኖራቸውን ቁርኝት ይበልጥ እንዲጠናከር መሆኑን አስታውቋል፡፡  

ዩኒቨርሰቲው በነገው እለት በሚያስጀምረው የቁርኣን ጥናት ቀን ተማሪዎች በየዕለቱ በቁርኣን ንባብ ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ ለማሳደግ ያግዛቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቀው ተነግሯል፡፡ አል አዝሃር በሚያዘጋጀው የቁርኣን ጥናት ቀን፤ ከግብጽ የተለያዩ ግዛቶች የሚሰባሰቡ ከ6 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ይሳተፋሉ አንደሚሳተፉ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአል አዝሃር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍሎች ኃላፊ የሆኑት ሸይኽ አይመን አብዱልገኒ እንደለጹት፤ በዩኒቨርሲቲው የሚከበረው የቁርኣን ጥናት ቀን ለሙሉ ቀን የከበር ነው፡፡ ዚህ ዝግጅት ላይ ከተለያዩ ግዛቶች የተሰባሰቡ ሁሉም ተማሪዎች በቃላቸው ያጠኑትን የቁርኣን ክፍል ለመምሕራን አልያም ለአስጠኚዎች ያቀርባሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular