እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናበአፋር እና ሶማሌ መካከል ማኅበረሰብ አቀፍ ዕርቀ ሰላም የማካሔድ እቅድ መያዙን የሰላም...

በአፋር እና ሶማሌ መካከል ማኅበረሰብ አቀፍ ዕርቀ ሰላም የማካሔድ እቅድ መያዙን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ

በወንድማቾቹ አፋር እና ሶማሌ ክልሎች መካከል ማኅበረሰብ አቀፍ ዕርቀ ሰላም የማካሔድ እቅድ መያዙን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ከክልሎች የተውጣጣ ልዑክ በአዋሳኝ አካባቢዎች በመገኘት የአፋር እና ሶማሌ ክልል ሰምምነት አፈጻጸም ላይ ግምገማ ማካሔዱ ተገልጿል፡፡

በአፋር እና ሶማሌ መካከል ማኅበረሰብ አቀፍ ዕርቀ ሰላም የማካሔድ እቅድ መያዙን የሰላም ሚኒስቴር ያስታወቀው ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 22/2016 ነው፡፡ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም ይህንኑ እቅድ በዛሬው እለት ይፋ አድርገዋል ተብሏል፡፡

አቶ ብናልፍ ይህን የገለጹት፤ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት የተደረገውን ስምምነት የአፈጻጸም ሁኔታ በሰላም ሚኒስትሩ አስተባባሪነት ከፌዴራልና ከክልሎች የተውጣጣ ልዑክ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች በመገኘት በገመገመበት ወቅት መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዚህ የግምገማ መርሐ ግብር በአካባቢው የነበሩ ግጭቶችን ለማስቆም የተደረገውን ስምምነትና የቴክኒክ ኮሚቴው የሥራ አፈጻጸም በጥልቀት ግምገማ እንደተደረገበት የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል፡፡ አጠቃላይ ሒደቱንና የግምገማውን ውጤት አስመልክቶ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም፤ ክልሎቹ ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም በደረሱት ስምምነት መሠረት ወደ ተግባራዊ የመፍትሔ እንቅስቃሴ መገባቱን መናገራቸውም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

በሁለቱ ክልሎች መካከል የተደረሰው ስምምነት በሁለት ምዕራፍ የተከፈለ መሆኑ ሲገለጽ፤ ቀዳሚው ምዕራፍ ግጭትና ሰብዓዊ ጉዳትን ማስቆም እንዲሁም በግጭቱ ሳቢያ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው መመለስ የሚለው ደግሞ በሁለተኛነት ተቀምጧል፡፡

አቶ ብናልፍ በሁለቱም ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎችን ከታጠቁ ኃይሎች እንቅስቃሴ ነፃ በማድረግ የፌዴራል የፀጥታ ኃይል ማሰማራት አንዱ የስምምነቱ አካል መሆኑን ማንሳታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በእነዚህ የስምምነት ማዕቀፎች መሠረትም የአተገባበሩን ሁኔታ የሚገመግም አካል ወደ ሥፍራው መሰማራቱን ጠቁመዋል ተብሏል፡፡

ከፌዴራል ተቋማት፣ ከፀጥታ ኃይሎችና ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጣ ልዑክ የስምምነቱን የመጀመሪያ ምዕራፍ አፈጻጸም መሬት ላይ ወርዶ ስለመገምገሙ ያነሱት ሚኒስትሩ፤ በግምገማው መሠረትም በአካባቢው መከላከያና ሌሎች የፌዴራል ፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ግዴታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።

የአካባቢው ሕዝብና የሁለቱም ክልሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮች ለዘላቂ መፍትሔ በትጋትና በባለቤትነት እየሰሩ መሆኑንም በቀጥታ አረጋግጠናል ነው ያሉ ሲሆን፣ በአካባቢው የነበሩ ግጭቶች መቆማቸው የአካባቢው ማኅበረሰብ በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ ህይወታቸውን መምራት መጀመራቸውን ጠቅሰው፤ ይኸው መልካም ጅምር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በግምገማው መሠረት የሰላም ሂደቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በስኬት በመጠናቀቁ ወደ ምዕራፍ ሁለት ትግበራ መሸጋገር የሚያስችል ሁኔታ ላይ መሆኑን የገለጹት ብናልፍ፤ በስምምነቱ ቀጣይ ምዕራፍም ግጭቶች በዘላቂነት በመፍታት ማኅበረሰብ አቀፍ ዕርቀ-ሰላም ማካሄድ እና ተፈናቃይ ወገኖችን በሙሉ ወደ ቀያቸው መመለስ መሆኑን ጠቁመዋል።

አፋር እና ሶማሌ ክልሎች ባለፈው ሐምሌ ወር በርእሰ መስተዳድሮቻቸው በኩል በአዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት የተስማሙት ባለፈው ሐምሌ ወር ነበር፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular