እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናኡስታዝ አቡበከር አሕመድ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ተደርገው...

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ

ዕውቁ የእስልምና መምሕር አቡበከር አሕመድ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ተደርገው ተሾመዋል፡፡ ለኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ሹመቱን የሰጡት ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም የፈረሙበትና “ሚንበር ቲቪ” የተመለከተው ደብዳቤ፤ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ተደርገው የተሾሙት ባላቸው ልምድና ተመክሮ “በጠቅላይ ምክር ቤቱ ያሉትን ክፍተቶች እንዲያሟሉ” ነው፡፡

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ተደርገው የተሾሙት ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፤ ከዚህ ሹመት አስቀድሞ የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ ሆነው ሲሠሩ የቆዩ ናቸው፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኃላፊነት ከመሥራታቸው በፊት፤ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና ኃላፊነቶች በንቃት በመሳተፍ ይታወቃሉ፡፡

ለኡስታዝ አቡበከር አሕመድ አዲስ ሹመት የሰጡት ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሚመሩት ምክር ቤት፤ በቀጣዩ 2017 ምርጫ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይኸው ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ እንደሚከናወን የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ ከሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮ ጠቅላይ ምክር ቤት በሐምሌ 2016 አዳዲስ አመራሮች ወደ ሥልጣን ሲመጡ የተቀመጠላቸው የሥልጣን ጊዜ ሦስት ዓመት መሆኑም የሚታወቅ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular