Homeዜናና ወቅታዊዜናግብጻዊው ኮሜዲያን ባሲም ዩሱፍ “በደኅንነት ሥጋት” ምክንያት የኤክስ አካውንቱን ማጥፋቱን ገለጸ

ግብጻዊው ኮሜዲያን ባሲም ዩሱፍ “በደኅንነት ሥጋት” ምክንያት የኤክስ አካውንቱን ማጥፋቱን ገለጸ

ለፍልስጤማዊያን በሚሰጠው ድጋፍ የሚታወቀው ግብጻዊው ኮሜዲያን ባሲም ዩሱፍ፤ “በደኅንነት ሥጋት” ምክንያት ኤክስ የተሰኘውን የማኅበራዊ ትስስር መድረክ አካውንቱን ማጥፋቱን ገልጿል፡፡ ባሲም ዩሱፍ ማብራሪያውን የሰጠው በኢንስታግራም ገጹ ነው፡፡

የግብጻዊው ኮሜዲያን ምላሽ የመጣው ከሁለት ቀን በፊት “ፀረ ሴማዊነት” አላግባብ ሰዎችን ፀጥ ለማሰኘት እንዲሁም ለማሸማቀቅ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው የሚል ጽሑፍ ካሰፈረ በኋላ፤ የአካውንቱ ደብዛ መጥፋቱን ተከትሎ፤ ኩባንያው አካውንቱን ሠርዞታል የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡

ባሲም ዩሱፍ በመጨረሻ በገጹ ላይ ባሠፈረው ጽሑፍ፤ በፅዮናዊያን አላግባብ ሰዎችን ፀጥ ለማሰኘት እንዲሁም ለማሸማቀቅ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ስላለው “ፀረ ሴማዊነት”፤ ተከታዮቹ ሐሳባቸውን እንዲሰጡት መጠየቁም ኩባንያው ለፍልስጤም ድጋፍ በመስጠት የሚታወቀው ግብጻዊ በኩባንያው ርምጃ ተወስዶበታል የሚል አስተያየት እንዲሠነዘር አድርጓል፡፡

ሆኖም ባሲም ዩሱፍ፤ 12 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት አካውንት እንዳይታይ የሆነው፤ እርሱ በደኅንነት ሥጋት ስላጠፋው መሆኑን አስረድቷል፡፡ ግብጻዊው ኮሜዲያን በቀጣይ ወደ ኤክስ የመመለስ ዕድል ይኑረው ወይም አይኑረው አሁን ማወቅ እንደማይቻል የገለጸ ሲሆን፣ የቅርብ ሰዎቼን ጭምር “አሳስቧል” ስላለው “የደኅንነት ሥጋት” ማብራሪያ ከመስጠትም ተቆጥቧል፡፡

የባሲም ዩሱፍን አካውንት አጥፍቷል በሚል በተጠቃሚዎቹ ተቃውሞ ሲቀርብበት የነበረው ኤክስ ኩባንያ፤ እስካሁን ድረስ ስለተፈጠረው ጉዳይ ምንም እስካሁን ድረስ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡

በዜግነት አሜሪካዊው የግብጽ ተወላጅ ባሲም ዩሱፍ፤ በተለይ በተያዘው ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ እስራኤል በጋዛ መሰንዘር የጀመረችውን ጥቃት ተከትሎ፤ ከብሪታኒያዊው ጋዜጠኛ ፒርስ ሞርጋን ጋር ባደረገው ስላቅ የሞላው ቃለ ምልልሱ ይበልጥ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ለመሳብ ችሎ ነበር፡፡ ባሲም በዚህ ቆይታው የእስራኤልን ጥቃት በፅኑ በማውገዝ፤ ለፍልስጤማዊያን ድምጽ ሆኗል በሚል ሙገሳ የሚቀርብለት ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular