የምሥራቅ አፍሪካዋ ሀገር ታንዛንያ፤ በቀጣዩ መስከረም ወር የአፍሪካ ሴቶች የቁርኣን ውድድር እንደምታስተናግድ ታውቋል፡፡ የቁርኣን ውድድሩን የምታስተናግደው ከተማ ዳሬሰላም እንደምትሆንም አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡
በዳሬሰላም በሚካሄደው የቁርኣን ውድድር ይፋ የተደረገው፤ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ሀገር አቀፍ የሴቶች የቁርኣን ውድድር ላይ ነው፡፡ የውድድሩ አዘጋጆች 11 የአፍሪካ ሀገራት እንደሚሳተፉ ቢገልጹም፤ በቁርኣን ውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ሀገራትን ዝርዝር እስካሁን ድረስ አላደረጉም፡፡
ከዚህ አስቀድሞ በታንዛንያ ባለፈው ሳምንት በተካሄደ ሀገር አቀፍ የቁርኣን ውድድር፤ በስምንት ዘርፍ በርካታ ሴት ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በቁርኣን ሒፍዝ የተከናወነው ውድድሩ፤ በአንድ ጁዝ፣ በሦስት ጁዝ፣ በአምስት ጁዝ፣ በአስር ጁዝ፣ በ15 ጁዝ፣ በ20 ጁዝ፣ በ25 ጁዝ እና በ30 ጁዝ የተደረገ ነበር፡፡
ታንዛንያ በተያዘው ዓመት በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የቀርኣን ውድድር አስተናግዳ ነበር፡፡ ሀገሪቱ በረማን ወር ባከናወነችው የቁርኣን ውድድር ላይ አሸናፊ የሆነው ሞሮኳዊው የቁርኣን መምሕር ኢልያስ አል ማሐያዊ ነበር፡፡ ሞሮኳዊው መምሕር ባሸነፈበት የቁርኣን ውድድር ላይ ከ500 በላይ ተወዳዳሪዎች ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በወቅቱ ውድድር የግብጽ እና አራን ተወዳዳሪዎች ሁለተኛ እና ሦስተኛደረጃ አግኝተው አጠናቀዋል፡፡
በቀጣዩ ወር የሴቶች የቁርኣን ውድድር የምታደርገው ታንዛንያ፤ ከአጠቃላይ ሕዝቧ የሙስሊሞች ቁጥር 34 በመቶ ይገመታል፡፡ በሀገሪቱ ከሚገኙ ሙስሊም ነዋሪዎች መካከል በርከት ያሉት የሚኖሩት በባር ዳርቻዎች አካባቢ መሆኑ ይነገራል፡፡ ከዚህ ውስጥ በርካታውን የሙስሊሞች ቁጥር የያዘችው ከፊል ራስ ገዟ ዛንዚባር ነች፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












