Homeዜናና ወቅታዊዜናየሐጅ መስተንግዶን ለግል ኤጀንሲዎች ለማስተላለፍ በፕሬዝዳንቱ የቀረበው ምክረ ሐሳብ ውድቅ መደረጉን ምክር...

የሐጅ መስተንግዶን ለግል ኤጀንሲዎች ለማስተላለፍ በፕሬዝዳንቱ የቀረበው ምክረ ሐሳብ ውድቅ መደረጉን ምክር ቤቱ ገለጸ

የኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ የሐጅ መስተንግዶን ለግል ኤጀንሲዎች ለማስተላለፍ በፕሬዝዳንቱ የቀረበ ምክረ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ ውድቅ መደረጉን ገልጿል፡፡ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ያቀረቡት ምክረ ሐሳብ ውድቅ ተደርጓል የተባለው በክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች ነው፡፡

ምክር ቤቱ የሐጅ መስተንግዶን ለግል ኤጀንሲዎች ለማስተላለፍ በፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም የቀረበው ሐሳብ ውድቅ አድርጓል የተባለው፤ ትናንት ነሐሴ 11/2016 ነው፡፡ ምክረ ሐሳቡን ያቀረቡት ፕሬዝዳንቱ የሐጅ መስተንግዶ ሥራ ለግል ኤጀንሲዎች መተላለፉ የሚኖረውን አሉታዊ እና አዎንታዊ ገጽታዎችን በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡

በዚሁ ገለጻ ወቅት የሐጅ ሥራ ለግል ኤጀንሲዎች ቢሰጥ፤ ኤጀንሲዎች የገንዘብ አቅም ስለሚኖራቸው የውጭ ምንዛሬ “ፍለጋው ጭንቀት ውስጥ የሚከታቸው አይሆንም” ማለታቸው ተገልጿል፡፡ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ኤጀንሲዎቹ በሑጃጅ ተመራጭ ለመሆን በሚያደርጉት ውድድር የተሻለ መስተንግዶ ሊመዘገብ እንደሚችልም ጠቁመዋል ተብሏል፡፡

እንደ ምክር ቤቱ መረጃ ፕሬዝዳንቱ መስተንግዶውን የግል ኤጀንሲዎች ቢሠሩትም፤ ጉዳዩ የሃይማኖት በመሆኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ አስፈላጊ ደንብና መመሪያዎችን በማውጣት ሥራቸውን በበላይነት የመቆጣጠር ኃላፊነት እንደሚኖረው ተናግረዋል። ሆኖም በፕሬዝዳንቱ የቀረበው ምክረ ሐሳብ በክልል የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች ተቃውሞ ገጥሞት ውድቅ መደረጉም ተመላክቷል፡፡ የክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች የፕሬዝዳንቱን ምክረ ሐሳብ ውድቅ ለማድረጋቸው ያቀረቡት ምክንያት አልተጠቀሰም፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዐቢይ ኮሚቴ የ1445 ዓ.ሂ የሐጅ መስተንግዶ ሥራ ክንውን ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular