Homeዜናና ወቅታዊዜናየኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የወደብ ውይይት ለሦስተኛ ዙር ተቀጠረ

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የወደብ ውይይት ለሦስተኛ ዙር ተቀጠረ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክዬ አደራዳሪነት ያደረጉት ሁለት ዙር ውይይት፤ ባለ መሥማማት መጠናቀቁን ተከትሎ ድርድሩ ለሦስተኛ ዙር ተቀጠረ፡፡ በአንካራ የተከናወነው ውይይት በቀጣይ ወር ይቀጥላል ተብሏል፡፡

በቱርክ አሸማጋይነት እየተካሄደ የሚገኘው ውይይት በቀጣዩ መስከረም ወር መጀመሪያ እንደሚቀጥል የተናገሩት የቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐካን ፊዳን ናቸው፡፡ ሐካን ፋይደን ይህን የተናገሩት በሀገራቸው አደራዳሪነት ለሚካሔደው የወደብ ውይይት አንካራ ያመሩትን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አፅቀሥላሴ እና የሶማሊያ አቻቸው አሕመድ ሙዓሊም ፈቂን ካነጋገሩ በኋላ ነው፡፡  

የቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐካን ፋይደን የሁለቱን ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማደራደር የጀመሩት ሰኞ ሐምሌ 6/2016 ነበር፡፡ ሐካን ፋይደን ሰኞ በነበረው ውይይት ሁለቱን ሚኒስትሮች አነጋግረው የነበረው በተናጠል የነበረ ቢሆንም፤ በቀጣይ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡ የቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዚህ ውይይት ላይ እንደ ውይይት መሻሻሎች  የታዩበት እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

የቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐምሌ 7/2016 ምሽት በሰጡት መግለጫ ልዩነቶችን ለመፍታት እንዲሁም ሊያስማሙ የሚችሉ መንገዶችን ለመፈለግ ጥረት መደረጉንም አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ያደረጉት ሁለተኛ ዙር ውይይት ከመካሄዱ አስቀድሞ ሀገራቱ በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ባለማሳየታቸው ለውጥ ይታበታል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ ሐካን ፋይደን ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት መግለጫ የተናገሩት ይህንኑ ግምት የሚያረጋግጥ ሆኗል፡፡

ከውይይቱ በኋላ ኢትዮጵያን በዋናነት የወከሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አፅቀሥላሴ፤ ቱርክ የጀመረችው ጥረት ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ያላትን ሕጋዊ ፍላጎት ያሳካል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ልዩነቶችን ለመፍታት እና ከሶማሊያ ጋር ያላትን  ግንኑኘነት ቀድሞ ወደነበረበት ለመመስለስ ዝግጁ መሆኗን በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ያካሄዱት ሁለተኛው ዙር ውይይት ቀድሞ በተያዘለት ቀጥሮ ሊከናወን የነበረው ከሦስት ሳምንት በኋላ የነበረ ቢሆንም፤ በስምምነት ቀኑ ወደፊት መጥቷል፡፡ የስምምነቱ ቀን ወደፊት ከመምጣቱ አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ጋር በስልክ ተነጋግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርዶጋን ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አረጋግጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ውይይት የ120 ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር ለሆነችው ኢትዮጵያ፤ “በጋራ ስምምነት መንገድ የባሕር በር የማግኘት” አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ተብሏል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular