Homeዜናና ወቅታዊዜናኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በወደብ ጉዳይ የሚያደርጉት ውይይት በነገው እለት ሊካሔድ ነው

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በወደብ ጉዳይ የሚያደርጉት ውይይት በነገው እለት ሊካሔድ ነው

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በወደብ ጉዳይ የሚያደርጉት ውይይት በነገው እለት በቱርክ እንደሚካሄድ ተሠምቷል። ነገ ሰኞ ነሐሴ 6/2016 በአንካራ የሚያካሔደውን ውይይት የምትመራው ቱርክ መሆኗ ታውቋል።

ለሁለተኛ ጊዜ የሚከናወነው የሁለቱ ሀገራት ውይይት፣ የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐካን ፋይደን አዲስ አበባ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ የሚደረግ ነው።

የቱርክ መገናኛ ብዙኃን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የሚያካሔዱት ውይይት ከስምምነት ይደረስበታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ሰኔ 24/2016 ፊት ለፊት ባይነጋገሩም ልዩነቶቻቸውን በሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ለመፍታት ቅን፣ ልባዊ እና ወደፊት የሚመለከት የሐሳብ ልውውጥ ማድረጋቸው ተነግሮ ነበር፡፡ በወቅቱ ኢትዮጵያን በመወከል አንካራ ያመሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀሥላሴ ናቸው፡፡ ሶማሊያም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን አሕመድ ሙዓሊም ፈቂን ለድርድር ልካለች፡፡ 

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጀመሪያውን ድርድር በተመለከተ ባወጣው አጭር መግለጫ፤ በውይይቱ “ግልጽ እና ወዳጅነት የተሞላበት የሐሳብ ልውውጥ” ተደርጓል ብሎ ነበር ያለ ቢሆንም ስለ ነገው ውይይት እስካሁን ያለው ነገር የለም።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular