Homeዜናና ወቅታዊዜናቢላል ማይክሮ ፋይናንስ ሥራ ጀመረ

ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ ሥራ ጀመረ

ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በይፋ ሥራ አስጀመረ። ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጠው የማይክሮ ፋንናንስ ተቋም፣ ሥራ ያስጀመረውን ቅርንጫፍ ኢሕሳን የሚል ሥያሜ ሰጥቶታል።

ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 የመጀመሪያ ቅርንጫፉን ሥራ ያስጀመረው ተቋሙ፣ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን የከፈተው በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነው።

ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ ሙሉ ለሙሉ ሸሪዐውን መሠረት በማድረግ የሚንቀሳቀስ ነው። የፋይናንስ ተቋሙ የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ ፍቃድ የወሰደው በተያዘው ዓመት የካቲት ወር ነበር።

በዛሬው እለት በተከናወነው የሥራ ማስጀመሪያ የምርቃት ሥነ ሥርዐት ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኃላፊዎች እና የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋሙ ሥራውን ሲጀምር በተለይም ሴቶችና ወጣቶች በሸሪዐ መር እና ሁሉን አካታች የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት በከተማና በገጠር ያለውን ድህነት በመቀነስ ረገድ አስተዋጽኦ የሚበርከት ተልዕኮ ማስቀመጡን ገልጿል።

ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ በቁጠባ፤ የዋዲያ፣ ሙዳረባ ተቀማጭ እንዲሁም የሙዳረባ ኢንቨስትመንት አገልግሎት እንገሚሰጥ የገለፀ ሲሆን፣ በብድር ደግሞ የዱቤ ሽያጭን መሠረት የሚያደርገውን የሙራባሀ፣ በሽርክና የሚሠራውን የኢጃራህ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰጠውን የቃርዱልሐሰን አገልግሎት ማካተቱንም አሳውቋል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular