Homeዜናና ወቅታዊዜናኢንዶኔዥያ እና ሲንጋፖር በሐላል ኢንዱስትሪ በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢንዶኔዥያ እና ሲንጋፖር በሐላል ኢንዱስትሪ በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

በደቡብ ምስራቅ እስያ ውስጥ የሚገኙት ኢንዶኔዥያ እና ሲንጋፖር፤ በሐላል ኢንዱስትሪ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ሁለቱ ሀገራት ስምምነቱን የተፈራረሙት በሲንጋፖር ነው፡፡

በሲንጋፖር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተከናወነው ሥነ ሥርዐት የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል በቀጣይ የሚከናወነውን የሐላል ግብይት ያቀላጥፋል ተብሏል፡፡ የሁለቱን ሀገራት የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት የኢንዶኔዥያ የሃይማኖት ጉዳዮች ምክር ቤት የሐላል ምርቶች ማረጋገጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሙሐመድ አቂል ኢርሃን እና የሲንጋፖር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከዲን መይዳን ናቸው፡፡

ከሁለት ወራት በኋላ በጥቅምት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው የመግባቢያ ስምምነት፤ የሁለቱን አገራት የሐላል የምስክር ወረቀቶች እና አርማዎች እውቅና እንዲሰጡ የሚያስችል ነው፡፡ ይህ ስምምነት ከኢንዶኔዥያ የሐላል ማረጋገጫ የተሰጣቸው ምርቶች ወደ ሲንጋፖር ገበያ እንዲገቡ እንዲሁም ከሲንጋፖርም እንዲሁ ወደ ኢንዶኔዠያ እንዲገቡ ያደርጋል ተብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አዲስ የሁለትዮሽ የንግድ ዕድሎችን ይከፍታል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ከሁለቱ ሀገራት መካከል ሲንጋፖር ከኢንዶኔዥያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከማድረጓ አስቀድሞ ከሌሎች ጋር ውል ፈጽማለች፡፡ ከእነዚህ ሀገራት ውስጥ ሳዑዲ ዐረቢያ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች፣ ዮርዳኖስ እና ሞሮኮ ይጠቀሳሉ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኘው ሐላል ኢንዱስትሪ ሰባት ዘርፎችን የሚያቅፍ ነው፡፡ ኢንዱስትሪው በሥሩ እስላማዊ ፋይናንስ፣ ሐላል ምግብ፣ ሐላል ፋሽን፣ ሐላል ሚዲያ እና መዝናኛ፣ የመድኃኒት እና ሐላል መዋቢያዎችን ያካትታል፡፡ ኢንዱስትሪው በዓለም አቀፉ 2.3 ትሪሊዮን ዶላር ገንዘብ እንደሚያንቀሳቅስ ይገመታል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular