የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል ከኃላፊነት ለቀዋል መባሉን አስተባበሉ፡፡ አቶ ሪያድ በሥራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ ለ”ሚንበር ቲቪ” ተናግረዋል፡፡
የሥራ አስኪያጁ ማስተባበያ የመጣው አቶ ሪያድ ጀማል ከአስር ቀናት በፊት ከከተማው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መልቀቃቸውን የጠቀሱበት ደብዳቤ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ከተሠራጨ በኋላ ነው፡፡ ሆኖም አቶ ሪያድ ስለ ደብዳቤው እና ይዘቱ በ”ሚንበር ቲቪ” ለቀረበላቸው ጥያቄ “ትክክለኛ አይደለም” ሲሉ መልሰዋል፡፡
የምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል በአሁኑ ሰዓት በሥራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስኪያጁን መልቀቅ ወይም አለመልቀቅ በተመለከተ ያለው ነገር የለም፡፡ (ሚንበር ቲቪ)