Homeዜናና ወቅታዊዜናበገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ሊተገብር መሆኑን መንግሥት አስታወቀ

በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ሊተገብር መሆኑን መንግሥት አስታወቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሬ ሊተገብር መሆኑን ያስታወቀው ዛሬ እሑድ ሐምሌ 21/2016 ነው።

መንግሥት ይህን የገለጸው ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ መግባቷን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዐት፣ የውጭ ምንዛሪ በገበያው አማካኝነት እንዲበየን የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል። ውሳኔውን ይፋ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማረጋገጥ በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል ይረዳል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የገቢ እና ወጪ ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ዋጋ ከገበያ እውነታዎች ጋር እንዲጣጣም የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ ስትገባ ከዓለም ዐቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት ከፋይናንስ ተቋማት በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ በርካታ ቢሊዮን ዶላር እንደምታገኝ ገልፀዋል።

መንግሥት የሚተገብረው በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን፣ የሀገሪቱን ይፋዊ መገበያያ ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን የሚቀይር ነው።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የምተገብረውን ይህን ሒደት በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዝርዝር መረጃ ይሰጣሉ ተብሏል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular