Homeዜናና ወቅታዊዜናየኢትዮጵያ ንግድ ባንድ ባንክ በወለድ ነጻ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ 90 ሚሊዮን ዶላር...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንድ ባንክ በወለድ ነጻ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ 90 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አገኘ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 በጀት ዓመት በወለድ ነጻ አግልግሎት 90 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱ ታወቀ፡፡ ባንኩ “ሲቢኢ ኑር” በሚል በሰየመው በዚህ አገልግሎት በኩል ያገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ፤ ከቀዳሚው ዓመት ከሦስት እጥፍ በላይ ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡

ባንኩ በሲቢኢ ኑር በኩል ያገኘው ከፍተኛ መሆኑ የተገለጸው፤ የ2016 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ እያካሄደ ባለው ግምገማ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ ከወለድ ነጻ አገልግሎቱ 90 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ቢያገኝም አጠቃላይ ያገኘው የውጭ ምንዛሬ ግን ዝቅ ማለቱ ታውቋል፡፡

ባንኩ ባለፈው ዓመት በአጠቃላይ ያሰባሰበው የውጭ ምንዛሪ 3.5 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ በተያዘው ዓመት በ300 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ቅናሽ እያሳየ ለመምጣቱ ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የተጠቀሰው፤ ከወጭ ንግድ የሚያገኘው የውጭ ምንዛሪ ዝቅ እያለ በመምጣቱ ነው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ ባገኘው የውጭ ምንዛሪ ቅናሽ ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ከኢትዮጵያ ባንኮች ከፍተኛውን ተተማጭ ያስመዘገበ ነው፡፡ ባንኩ ከወለድ ነጻ ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ከ115 ቢሊዮን ብር ተሻግሯል፡፡

የአስቀማጭ ደንበኞችን ቁጥር በተመለከተም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወለድ ነፃ እያስቀመጡ ያሉ ደንበኞች ቁጥር 7.2 ሚሊዮን በላይ ደርሷል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በመስኮት ደረጃ የሚሰጡ ከሃያ በላይ ባንኮች ይገኛሉ፡፡ ከባንኮቹ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ አራት ባንኮች በኢንዱስትሪው ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

የተቀማጭ ገንዘብ መጠናቸው በየዓመቱ በአማካይ 24 በመቶ እያደጉ የመጡት ባንኮቹ፤ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 222.8 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰባቸው ይገለጻል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular