Homeዜናና ወቅታዊዜናአማና ሞዴል ት/ቤት በሚቀበላቸው ተማሪዎች የክፍል እርከን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ

አማና ሞዴል ት/ቤት በሚቀበላቸው ተማሪዎች የክፍል እርከን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ

በአንጋፋ የዩኒቨርሲቲ ምሑራን እና ባለሐብቶች ጥምረት የተቋቋመው አማና ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ በሚቀበላቸው ተማሪዎች የክፍል እርከን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ። ት/ቤቱ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንደሚቀበል ተገልጿል።

አዲሱ አማና ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ውሳኔ ማሳለፉን ያስታወቀው ዛሬ እሑድ ሐምሌ 7/2016 ነው።

ከሁለት ሳምንት በፊት ሰኔ 27/2016 በይፋ ሥራ የጀመረው ትምህርት ቤቱ፣ በ2017 የትምህርት ዘመን ለመቀበል በእቅድ ያስቀመጠው የዘጠነኛ እና አስረኛ ክፍል ተማሪዎችን ቢሆንም፣ በሌሎች የክፍል እርከኖች እንዲያስተምሩ ፍላጎት መኖሩን የአማና ትምህርት ቤት የአካዳሚክ ቦርድ አባል የሆኑት አቶ አልዩ ሰዓድ ለሚንበር ቲቪ ተናግረው ነበር።

ትምህርት ቤቱ ዛሬ እንዳስታወቀው፣ ለ2017 የትምህርት ዘመን የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንዲቀበል ውሳኔ አሳልፏል።

የአማና ሞዴል ትምህርት ቤት ኃላፊዎች ለውሳኔው መነሻ ሆኖናል ያሉት “ጥቂት ከማይባሉ የተማሪ ወላጆች የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስመዝገብ ጥያቄ መቅረቡን” ነው።

ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ለ2017 የትምህርት ዘመን የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ሲወስን ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል። ትምህርት ቤቱ ተመዝጋቢ ተማሪዎች የትምህርት አቀባበል ዝግጁነታቸውን ለመመዘን የሚያስችል የመግቢያ ፈተና ይወስዳሉ ብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሥራውን በይፋ የጀመረው አማና ሞዴል ትምህርት ቤት መሥራቾች፣ ትምህርት ቤቱን ከመክፈታቸው በፊት አማና የወጣቶች ልማት ኔትወርክ የተሰኘ የሰቪል ማኅበረሰብ ድርጅት አቋቁመው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው፡፡

ድርጅቱ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተፈጥሮ ሣይንስ መምህራን የሣይንስ ትምህርቶችን በተግባር አስደግፎ በማስተማር ላይ ያተኮረ ነጻ የሥልጠና መርሐ ግብር ሲያካሔድ መቆየቱም በምረቃ መርሐ ግብር ላይ ተገልጿል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular