Homeዜናና ወቅታዊዜናየስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ነጥብ ታወቀ

የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ነጥብ ታወቀ



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ነጥብ አደረገ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ ያደረገው በዛሬው እለት ነው፡፡

ዛሬ ዐርብ ሐምሌ 5/2016 ይፋ በተደረገው የቢሮው መረጃ መሠረት፤ የ2016 የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ነው። በአንፃሩ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45 መሆኑንም የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በዘንድሮው ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ብዛት 85 ሺህ 219 ነው። እነዚህ ተማሪዎች በመደበኛ እንዲሁም በማታ ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡

ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 67 ሺሕ 903 የሚሆኑት ማለትም 78.9 በመቶ ያህሉ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

የ2016 የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለማስቻል መሆኑን የጠቆመው ቢሮው፣ በቀጣይ ጥቂት ቀናት የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ቢሮው የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ትክክለኛ ቀን አላሳወቀም፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular