እሑድ , محرم 8, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናበአዲስ አበባ ለሚካሔደው የቁርኣን ውድድር ዘጠኝ ዳኞች ተሠይመዋል ተባለ

በአዲስ አበባ ለሚካሔደው የቁርኣን ውድድር ዘጠኝ ዳኞች ተሠይመዋል ተባለበሳምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የቁርኣን ውድድር የሚዳኘው በኢትዮጵያዊያን እና ሞሮካውያን ዳኞች መሆኑ ታወቀ፡፡ ሞሮካውያን ዳኞች በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሞሮኮው ንጉሥ ሙሐመድ ስድስተኛ ፋውንዴሽን ጋር ጁመዓ ሐምሌ 5/2016 ለሚያካሔደው ሀገር አቀፍ የቁርኣን ውድድር፤ ዳኞችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ ውድድሩን እንዲዳኙ የመረጣቸው ዳኞች ብዛት ዘጠኝ መሆኑን የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር  ዓብደላ  ኸድር ለሚንበር ቲቪ ተናግረዋል፡፡

የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ፤ ከዳኞቹ ውስጥ ስድስቱ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሆኑ በመግለጽ፣ ቀሪዎቹ ሦስት ዳኞች ከሞሮኮ ይወከላሉ ብለዋል፡፡ ከስድስቱ ኢትዮጵያዊያን የቁርኣን ውድድሩ ዳኞች ውስጥ ሸይኽ ናስር ሙዘሚል፣ ሸይኽ ኢድሪስ ዓሊ፣ ሸይኽ ዓብዱረሕማን ኸጢብ፣ ሸይኽ ሰዒድ ዓሊ እና ሸይኽ ተውፊቅ ኑርገባ እንደሚገኙበት ዶክተር  ዓብደላ  ኸድር ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያዊኑ ውጪ ውድድሩን የሚዳኙት ሞሮካዊያ ዳኞች በዛሬው አለት ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ወደ አዲስ አበባ የገባውን የዳኞች ልዑካን ቡድን ዑስታዝ ዑስማን ሰቀሊ ሑሴን መርተውታል።

የፊታችን ጁመዓ በአንድ ቀን የሚጠናቀቀው ሀገራዊ የቁርኣን ውድድር በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽ/ቤት የተዘጋጀ ነው፡፡ ለአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የደረሱት ሐፊዞች በክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤቶች በተዘጋጁ ውድድሮች ተሳትፈው ያሸነፉ ናቸው ተብሏል፡፡

48 ተወዳዳሪዎችን የሚያሳትፈው ውድድር፣ በቀጣይ ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር መድረክ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚለዩበት እንደሚሆንም ተገልጧል፡፡

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የቁርኣን ውድድር ሁለት ዘርፎች ይኖሩታል፡፡ ከዘርፎቹ መካከል አንደኛው ሕግጋት ላይ መሠረቱን ሲያደርግ፣ ሁለተኛው ዘርፍ የቁርኣን ሂፍዝ ነው፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments