እሑድ , محرم 8, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናሚንበር ቲቪ በአዲስ ዓመት አዳዲስ ፕሮግራሞችን ሊጀምር ነው

ሚንበር ቲቪ በአዲስ ዓመት አዳዲስ ፕሮግራሞችን ሊጀምር ነው

  • እለታዊ መረጃዎች የሚያቀርቡበት “ሚንበር ኸበር” ዛሬ ምሽት ይጀምራል

በሚንበር መልቲ ሚዲያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ስር የሚተዳደረው ሚንበር ቲቪ፤ የአዲሱን የሂጅሪ ዓመት መግባት ተከትሎ ወደ ተመልካቾቹ አዳዲስ መሰናዶዎችን ሊያቀርብ ነው፡፡ በጣቢያው በአዲስ ዓመት ከሚጀመሩ መሰናዶዎች መካከል “ሚንበር ኸበር” ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 1/2016 ምሽት እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

ሚንበር ቲቪ በሂጅሪ ዘመን ቀመር መሠረት ከአዲስ ዓመት መግባት ጋር አዳዲስ መሰናዶዎችን ይዞ እንደሚቀርብ የገለጹት የጣቢያው የፕሮዳክሽን እና አርት ዳይሬክተር ሙሐመድ ፈረጅ ናቸው፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ከሆነ ጣቢያው ይዟቸው የሚቀርባቸው መሰናዶዎች ከዚህ ቀደም ተመልካቾች በለመዱት የጥራት ደረጃ ይሆናል፡፡

የፕሮዳክሽን እና አርት ዳይሬክተር ሙሐመድ ፈረጅ

ሙሐመድ ፈረጅ፤ ሚንበር ቲቪ በአዲሱ ዓመት ያቀርባቸዋል ካሏቸው መሰናዶዎች ውስጥ፣ ዛሬ ምሽት ይጀምራል ያሉትን እለታዊ መረጃ የሚቀርብበትን ሚንበር ኸበር ጠቅሰዋል፡፡ ሚንበር ኸበር ከሰኞ እስከ ዐርብ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ በሁሉም ክፍለ ዓለማት የሚገኙ ሙስሊሞች ማኅበራዊ፣ የምጣኔ ሐብት እንዲሁም አዳዲስ ክስተቶችን የሚይዝ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ሚንበር ኸበር በሀገር ውስጥ በተለይ ሙስሊም በዝ የሆኑ አካባቢዎችን ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው ተብሏል፡፡

ሚንበር ቲቪ ከመረጃ ከእለታዊ መረጃ በተጨማሪ “አንድ እንጀራ” የተሰኘ ማኅበራዊ ጉዳዮን የሚያነሳ መሰናዶ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል፡፡ ሙሐመድ ይህ መሰናዶ “አንድነታችን ላይ ያሉ መልኮቻችንን የምንዳስስበት ነው” ብለዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪም ሚንበር ቲቪ ዘጋቢ ፊልሞችን፣ ከእርቅ እና ይቅርታ ጋር የተገናኘ ሾው እንዲሁም የመስጂድ ዳዕዋ የሚቀርብበት “ሚንበሩል ዒልም” የጣቢያው አዳዲስ መሰናዶዎች እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡  

የፕሮዳክሽን እና አርት ዳይሬክተሩ፣ ከአዳዲሶቹ መሰናዶዎች በተጨማሪ ሚንበር ቲቪ ባለፈው በ1445 ዓ.ሂ በዋናነት በሚቀርብበት ቴሌቪዥን እንዲሁም በኦንላይን ከተመልካቾች ጋር የነበረውን መስተጋብር አብራርተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ከ500 ሺሕ በላይ ሰብስክራይበር ባለው በዩትዩብ አማራጭ ከ100 ሚሊዮን በላይ ዕይታ መቀዳጀቱንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጣቢያው የሚያቀርባቸው መሰናዶዎች ይበልጥ ተመልካቾችን የሚመጥን እንዲሆን የስቱድዮ ግንባታ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን አብራርተዋል፡፡

በእስላማዊ ጉዳዮች ላይ መሠረቱን ያደረገው ሚንበር ቲቪ፤ ከሦስተ ዓመት ከመንፈቅ በላይ በአየር ላይ ቆይቷል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments