እሑድ , محرم 8, 1446
Google search engine
Homeየቲቪ ፕሮግራሞችየኢትዮጵያ ሙስሊም ጤና ባለሞያዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ

የኢትዮጵያ ሙስሊም ጤና ባለሞያዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደየኢትዮጵያ ሙስሊም ጤና ባለሞያዎች ማኅበር የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ። ማኅበሩ ባዘጋጀው ጠቅላላ ጉባዔ በሙስሊም ጤና ባለሞያዎች መካከል የትውውቅ ፕሮግራም ተከናውኗል።
.
በአዲስ አበባ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል ትናንት እሑድ ሰኔ 30/2016 በተካሄደው የኢትዮጵያ ሙስሊም ጤና ባለሞያዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባዔ ላይ፣ ከተለያዩ የክልል ከተሞች የተውጣጡ ጤና ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ከምሥረታ አንስቶ የተከናወኑ ተግባራት ተዘርዝረዋል፡፡ የማኅበሩ ኃላፊዎች በዚሁ ወቅት ያለፉትን ወራት አባላት በማሰባሰብ ላይ መቆየታቸውን ገልጸው፣ ሌሎች ተግባራትንም ማከናወናቸውን አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡ ለጉባዔው ታዳሚያን በየማኅበሩ የተዘጋጀ ዶክመንተሪ ለዕይታ በቅቷል፡፡

እንደ ሙስሊም ጤና ባለሞያዎች ማኀበር ኃላፊዎች ከሆነ፣ በቀጣይ የማህበሩ አባላትን በማጠናከር በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ ሙስሊሞች የጤና ሕክምና እንዲያገኙ ለማስቻል እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች በዲን ዕውቀት ታንፀው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የተለያዩ እገዛዎችን ለማድረግ ማቀዱ በጉባኤው ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ጤና ባለሞያዎች ማኅበር የተመሠረተው በተያዘው ዓመት መጀመሪያ ላይ ነበር። ትናንት የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤም ይህንኑ ማብሰሪያ መሆኑ ተገልጿል።


RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments