እሑድ , محرم 8, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናበበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና ቀርቷል መባሉ ሐሰተኛ ነው ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና ቀርቷል መባሉ ሐሰተኛ ነው ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

የትምህርት ሚኒስቴር በዘንድሮው ዓመት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና እንደቀረ ተደርጎ እየቀረበ ያለው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ ነው ያለው በዛሬው እለት ነው።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ዐርብ ሰኔ 28/2016 ባወጣው አጭር መግለጫ፣ ፈተናው ሐሰተኛ ነው የተባለው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ነው ብሏል። እንደ መግለጫው ከሆነ ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጥ ይሆናል።

የትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች ይሄንኑ ተገንዝበው ዝግጅታችውን እንዲቀጥሉ ባሳሰበበት መግለጫው፣ ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው የ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ከትግራይ ክልል በስተቀር ፈተናው ከሐምሌ 3/2016 ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል።

በጊዜ ሠሌዳው ላይ እንደተቀመጠው በቀዳሚነት ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ለፈተና የሚቀመጡት የማኅበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች ናቸው። የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ይሰጣል።

በሁለት ዙር ፈተናው ይሰጥበታል በተባለው ትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ሐምሌ 2 ተጀምሮ ሐምሌ 12/2016 ይጠናቀቃል ተብሏል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ በ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 701 ሺሕ 489 ነው።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments