ሰኞ , محرم 9, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናዓመታዊው የበድር ዓለም አቀፍ ጉባዔ በዳላስ ተጀመረ

ዓመታዊው የበድር ዓለም አቀፍ ጉባዔ በዳላስ ተጀመረበድር ኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የበድር ዓለም አቀፍ ጉባዔ፤ በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ዳላስ ከተማ ተጀመረ፡፡ በጉባዔው ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ትናንት ሐሙስ ሰኔ 27/2016 የተጀመረው የበድር ዓለም አቀፍ ጉባዔ፤ “እስላማዊ መርሆች ላይ ፀንቶ መቆም” በሚል መሪ ቃል የሚከናወን መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ በቴክሳስ ዳላስ የሚካሄደው ጉባዔ በዘንድሮ ዓመት ለ24ኛ ጊዜ የሚካሔድ ነው፡፡ ትናንት ሐሙስ የተጀመረው ጉባዔ እስከ መጪው እሑድ ሰኔ 30/2016 ይቆያል ተብሏል፡፡

የጉባዔው አዘጋጅ በድር ኢትዮጵያ፤ አሜሪካ፣ ካናዳ እና አውሮፓን ጨምሮ 27 የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላትን የሚወክል ድርጅት ነው፡፡ ድርጅት ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚገኙ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች ወደ ዳላስ ከተማ ገብተዋል፡፡ ከውጪ ሀገራት ወደ ዳላስ ከተጓዙ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች በተጨማሪ ከኢትዮጵያ እንግዶች ተጋባዥ ሆነው ወደ አሜሪካ አቅንተዋል፡፡

ወደ አሜሪካ ከተጓዙት ውስጥ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይገኙበታል፡፡ ትናንት ሐሙስ በጉባዔው ክፈቻ ቀን ዳላስ የደረሱት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፤ ጉባዔውን ወደምታስናግደው ዳላስ ከተማ ሲደርሱ በጉባዔው አዘጋጆች አቀባበል እንደተደረገላቸው ምክር ቤቱ ያወጣው የፎቶ ግራፍ መረጃ አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ዳላስ ሲደርሱ

ትናንት ሐሙስ አሜሪካ ከገቡት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አስቀድሞ ዋና ጸሐፊው ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ፤ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሡልጣን አማን እንዲሁም የምክር ቤቱ አባል አቶ ሱፍያን ዑስማን ጋር ዳላስ ደርሰዋል፡፡

ሸይኽ ሡልጣን አማን፣ ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ እና አቶ ሱፍያን ዑስማን በአሜሪካ
 
 

በድር ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ዓመታዊ ጉባዔውን ያካሄደው በአሜሪካ ቨርጂንያ ግዛት ነበር፡፡ ድርጅቱ ከሁለት ዓመት በፊት 22ኛ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጉባዔውን አካሔዷል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments