እሑድ , محرم 8, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናጠቅላይ ሚኒስትሩ በነገው እለት በፓርላማ በመገኘት የፌዴራል መንግሥቱን የ2016 በጀት ዓመት የሥራ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በነገው እለት በፓርላማ በመገኘት የፌዴራል መንግሥቱን የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሊያቀርቡ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው እለት በፓርላማ በመገኘት የፌዴራል መንግሥቱን የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሊያቀርቡ ነው፡፡ ፓርላማው የፌዴራል መንግሥትን የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ ሰኔ 27/2016 የፌዴራል መንግሥትን የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እንደሚያፀድቅ ያስታወቀው በዛሬው እለት ነው፡፡

ነገ ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሚገኙበት የሚካሔደው 36ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ ከ2017 የፌዴራል መንግሥ በጀት በተጨማሪ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የሚሰጥበት ነው ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱ የ2017 የፌዴራል መንግሥት በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት የሚያፀድቀው፣ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55 (11) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 76 መሰረት ረቂቅ በጀቱን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ ካደመጠ በኋላ ነው፡፡

በምክር ቤቱ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments