እሑድ , محرم 8, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናየቆዳ በሽታ ለጋዛ ሕፃናት ፈታኝ እየሆነ መጥቷል ተባለ

የቆዳ በሽታ ለጋዛ ሕፃናት ፈታኝ እየሆነ መጥቷል ተባለ

በጋዛ በአደገኛ የቆዳ በሽታዎች የሚጠቁ ሕፃናት ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ፡፡ በፍልስጤም ግዛት ውስጥ ባለፉት አስር ወራት ከ150 ሺሕ በላይ ሰዎች በአደገኛ የቆዳ በሽታዎች መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

በጋዛ ለሕፃናት የቆዳ በሽታ መዛመት መንስኤ ሆኗል የተባለው፣ ንጽሕና ለመጠበቅ የሚውሉ ቁሳ ቀሶች ዕጥረት ነው ተብሏል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እስራኤል በጋዛ ከመስከረም የመጨረሻ ቀናት ወዲህ እየሰነዘረች በምትገኘው ጥቃት፣ በቆዳ በሽታ ከተጠቁ ከ150 ሺሕ በላይ ፍልስጤማዊያውን ውስጥ 97 ሺሕ ገደማ የሚሆኑት በእከክ ተለክፈዋል፡፡

አልጀዚራ ያናገራት ፍልስጤማዊቷ ዋፋ ኤልዋን እንደተናገረችው፣ በተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ አብሯት የሚገኘው የአምስት ዓመት ልጇ ሰውነቱን ሲያክ ነው የሚያድረው፡፡ ዋፋ በዚሁ ምክንያት የልጇ እጅ እና እግር መልኩን መለወጡን አስረድታለች፡፡

በመጠለያው ውስጥ መሬት ላይ እንደሚተኙ የምትገልጸው ፍልስጤማዊቷ ዋፋ ኤልዋን፣ ለልጇ የቆዳ ሕመም ሰበብ የሆነውም በመኝታቸው ስር የሚርመሰመሰው ተውሳክ መሆኑንም አብራርታለች፡፡ ዋፋ ኤልዋን አክላም አሁን በሚገኙበት መጠለያ ልጆችን እንደቀደመው ጊዜ ንጽሕናቸውን መጠበቅ አዳጋች መሆኑን በመጠቆም፣ በመጠለያው ሳሙና እና ሌሎች የንጽሕና መጠበቂያ ቁሶች እንደሌሉ ትገልጻለች፡፡

የፍልስጤም ሕፃናት በበሽታ እንዲጠቁ ምክንያት የሆነውን ጥቃት የምትሰነዝረው እስራኤል፤ ባለፉት አስር ወራት 38 ሺሕ ገደማ ፍልስጤማዊያንን ገድላለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በርካታ ቁጥር የሚይዙት ሕፃናት እና እናቶች ናቸው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments