Homeዜናና ወቅታዊዜናበድሬዳዋ ከተማ የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ማለዳ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ የእሳት አደጋው የተከሰተው በገበያ ሥፍራ መሆኑ ታውቋል፡፡

በከተማው ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በግምት 1፡45 የተከሰተው የእሳት አደጋ፣ እስከ ረፋድ ድረስ የቀጠለ እንደነበር ሚንበር ቲቪ ከከተማው ነዋሪ ሰምቷል፡፡ እንደ ነዋሪው ከሆነ አሸዋ ገበያ በተባለው ሥፍራ በሚገኙ ሱቆች ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ አምስት ሰዓት ገደማ በእሳት አደጋ ሠራተኞች እና በነዋሪዎች ርብርብ ሊገታ ቢችልም ሙሉ ለሙሉ አልቆመም፡፡

ከድሬዳዋ ከተማ የሚወጡ መረጃዎች በእሳት አደጋው ከአሸዋ ገበያ እስከ ታዋን (ሰልባጅ ተራ) ይገኙ የነበሩ ሱቆች እንዲሁም የቤት ዕቃ መሸጫ የሆነው የገበያ ማዕከል ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ የእሳት አደጋው ማሽላ ተራን በከፊል እንዳወደመም ታውቋል፡፡

የድሬዳዋ ከተንቲና ከድር ጁሐር እሳት አደጋው በተከሰተበት የገበያ ሥፍራ በተገኙበት ወቅት/SM

የእሳት አደጋው ከተከሰተ በኋላ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሐር አደጋው በደረሰበት የገበያ ሥፍራ ተገኝተው የደረሰውን ውድመት ተመለክተዋል፡፡ ከንቲባው የአደጋውን መንስኤና የጉዳት መጠን በምርመራ በማጣራት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ መናገራቸውን የከተማዋ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ በዛሬው እለት የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤ እንዲሁም የደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular