Homeዜናና ወቅታዊዜናየጤና ሚኒስቴር ለአሥር ቀናት የሚቆይ የክትባት ዘመቻ ይፋ አደረገ

የጤና ሚኒስቴር ለአሥር ቀናት የሚቆይ የክትባት ዘመቻ ይፋ አደረገ

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የክትባት ዘመቻ ይፋ ያደረገው በዛሬው እለት ነው፡፡ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 25/2016 ይጀምራል ያለው የክትባት ዘመቻ ለአሥር ቀናት የሚቆይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ኃላፊዎች እንደገለጹት፣ የክትባት ዘመቻው ክትባት ላልጀመሩ እና ጀምረው ላቋረጡ ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የሚሰጥ ነው፡፡

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ተደራሽ ይሆናሉ ለተባለበት የክትባት ዘመቻ፣ አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንም ሚኒስቴሩ ጠቀሟል፡፡

ዘመቻው የሚካሄድባቸው ከአንድ ሺሕ በላይ ወረዳዎች ተለይተዋል የተባለ ሲሆን፣ ለተፈናቃዮች፣ ወረርሽኝ ላለባቸው አካባቢዎች እና ራቅ ላሉ ወረዳዎች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውም ተገልጧል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በተለያዩ ጊዜያት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአምስት ዓመት በታች ላሉ ሕፃናት በሚሰጠው ክትባት ሕፃናት የፖሊዮ፣ የመንጋጋ ቆልፍ እና ሌሎች ከአስር በላይ የበሽታ መከላከያ ክትባቶችን እንደሚወስዱ የሚታወቅ ነው፡፡ ለሕፃናቱ የሚሰጠው ክትባት ሊያጋጠማቸው ከሚችለው አካል ጉዳት እና ከሕመም ለመታደግ የሚያስችል መሆኑን የጤና ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular