Homeዜናና ወቅታዊዜናከወለድ ነጻ ባንክ እና የተካፉል ፎረም በኢትዮጵያ ሊካሔድ ነው

ከወለድ ነጻ ባንክ እና የተካፉል ፎረም በኢትዮጵያ ሊካሔድ ነው

አዲስ አበባ ከተማ ዓለም አቀፍ ከወለድ ነጻ ባንክ እና የተካፉል ፎረም ልታስተናግድ ነው፡፡ ለአምስተኛ ጊዜ የሚከናወነው ከወለድ ነጻ እና የተካፉል ፎረም ላይ ከሃያ በላይ ሀገሮች የባንኩ ዘርፍ ተዋናዮች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

አምስተኛው ዓለም አቀፍ ከወለድ ነጻ ባንክ እና የተካፉል ፎረም፣ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሔድ ያስታወቀው ‘አልሑዳ ሴንተር ኦፍ ኢስላሚክ ባንኪንግ እና ኢኮኖሚክስ’ የተሰኘ ድርጅት ነው፡፡ በቀጣዩ ወር ከሐምሌ 18 እስከ 20/2016 የሚካሔደው ፎረም፣ በአዲስ አበባ ሐያት ሪጀንሲ የሚከነወን ይሆናል ተብሏል፡፡

ፎረሙ ከቀዳሚዎቹ ሁለት ቀናት ውሎ በኋላ በመጨረሻው ቀኑ ከወለድ ነጻ ባንክ እና የተካፉል አገልግሎት አሠራር ሒደት ላይ ወርክ ሾፕ እንደሚዘጋጅ አልሑዳ ሴንተር ኦፍ ኢስላሚክ ባንኪንግ እና ኢኮኖሚክስ አስታውቋል፡፡

ለሦስት ቀናት በሚቆየው ፎረም ላይ ከሌሎች ሀገሮች ከሚመጡ ተሳታፊዎች ውጪ በኢትዮጵያ ውስጥ ከወለድ ነጻ የባንክ እና ኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጡ የፋይናንስ ተቋማት ተወካዮች እንደገኙም አዘጋጁ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል፡፡

በዘንድሮው ፎረም ላይ በኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አገልግሎት የሚሰጡ ከሃያ በላይ የወለድ ነጻ ባንኮች ኃላፊዎች ይሳተፋሉ ነው የተባለው፡፡

አልሑዳ ሴንተር ኦፍ ኢስላሚክ ባንኪንግ እና ኢኮኖሚክስ ባወጣው መረጃ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ከወለድ ነጻ እና የተካፉል ፎረም፤ አንደኛው አላማ በዘርፉ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ላይ የተመዘገቡ አዳዲስ ጉዳዮች ላይ የልምድ ልውውጥ ማድረግ ነው፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ ዓለም አቀፍ ከወለድ አልባ ባንክ እና የተካፉል ፎረም አዘጋጅታለች፡፡ በፎረሙ ላይ የባንኩ ዘርፍ ተዋናዮች ተሳታፊ ሆነው ነበር፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አምስተኛውን ዓለም አቀፍ ከወለድ ነጻ ባንክ እና የተካፉል ፎረም የሚያዘጋጀው አልሑዳ ሴንተር ኦፍ ኢስላሚክ ባንኪንግ እና ኢኮኖሚክስ፤ በእስላማዊ ባንክ እና ፋይናንስ ዘርፍ በጥናት እና ምርምር ላይ የሚሠራ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ መቀመጫውን ያደረገው በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ዱባይ እና ፓኪስታን ላሆር ከተማ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular