Homeዜናና ወቅታዊዜናየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዋዲዓህ አገልግሎት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዋዲዓህ አገልግሎት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ


መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከዋዲአህ ተቀማጭ ሒሳብ አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ። ባንኩ ከዋዲዓህ የተቀማጭ ሒሳብ ላይ ገንዘብ በቅርንጫፍ ወጪ ለማድረግ ይከፈል የነበረውን ክፍያ እንዲቀር ማድረጉን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትናንት ሐሙስ ሰኔ 20/2016 ይፋ ባደረገው የታሪፍ ማሻሻያ፣ በቅርንጫፍ ከሚደረገው ወጪ በተጨማሪ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ላይ ማሻሻያ ያደረገበትን አዲስ ታሪፍ ይፋ አድርጓል፡፡

ባንኩ በዲጂታል ባንክ አገልግሎት በሞባይል ባንኪንግ ከሒሳብ ወደ ሒሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ፣ ከዚህ ቀደም በነፃ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት 3 ብር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚያስከፍል በማሻሻያው ላይ አስፍሯል፡፡ በሞባይል ባንኪንግ ወደ ዋሌቶች ከ10 ሺሕ ብር በላይ ለማስተላለፍ ቀድሞ ከነበረው የ10 ብር ታሪፍ ላይ 5 ብር በመጨመር የ15 ብር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚያስከፍል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወራት በፊት በመሳሳይ የአገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

መንግሥታዊው ንግድ ባንክ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ከ6.6 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ገልጧል፡፡ በተጨማሪም ከ2 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን በዘርፉ ማፍራት መቻሉን አስታውቋል፡፡ ባንኩ በ1 ሺ 936 ቅርንጫፎች በኩል የወለድ ነጻ ባንክ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ከእነዚህ 154 ቅርንጫፎች ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 1 ሺሕ 782 አገልግሎቱን በመስኮት ይሰጣሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular