Homeዜናና ወቅታዊዜናበመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች የጋዛን ሰቆቃ ለማስቆም እንዲረባረቡ ጥሪ ቀረበ

በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች የጋዛን ሰቆቃ ለማስቆም እንዲረባረቡ ጥሪ ቀረበ

የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ዓሊ አል ቀራዳጊ በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች የጋዛን ሰቆቃ ለማስቆም እንዲረባረብ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ዋና ጸሐፊው ሙስሊሞች የፍልስጤማዊያንን ሰቆቃ ኃላፊነታቸው ድርብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሸይኽ ዓሊ አል ቀራዳጊ ጥሪውን ያቀረቡት ለመላው ዓለም በተንቀሳቃሽ ምሥል ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ነው፡፡ የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት ዋና ጸሐፊ በመልዕክታቸው ሙስሊሞች ከፍልስጤማዊያን ጎን እንዲቆሙ ሃይማኖታዊ እና ሰብዓዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ሸይኽ ዓሊ በዚሁ ንግግራቸው በጋዛ የሚፈጸመውን ጥቃት ዓለም በዝምታ መመልከቱንም “አሳፋሪ ነው” ሲሉ ኮንነውታል፡፡

እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማዊያን ላይ ከመስከረም ወር መጨረሻ አንስቶ በምትሰነዝረው ጥቃት 37 ሺሕ 700 ንጹሐን ተገድለዋል፡፡ ከተገደሉት መካከል የእናቶች እና ሕፃናት ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡

በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች የጋዛ ሰቆቃ እንዲያበቃ እንዲረባረቡ ጥሪ ያቀረቡት ሸይኽ ዓሊ አል ቀራዳጊ በዋና ጸሐፊነት የሚሠሩበት የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት፣ ዋና መቀመጫውን ኳታር ዶሓ የደረገ ድርጅት ነው፡፡

የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት ከዚህ ቀደም በታላቁ ግብጻዊ የእስልምና ሃይማኖት ሊቅ ሸይኽ የሱፍ አል ቀርዳዊ ይመራ የነበረ ነው፡፡ ኅብረቱ ከመላው ዓለም ከ90 ሺሕ በላይ ሙስሊም ሊቃውንትን በአባልነት መያዙን በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular