በአዲስ አበባ ከተማ የልደት ካርድ ምዝገባ ቀን ላይ ማሻሻያ እንደተደረገ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ። ተገልጋዮች በሚኖሩበት ወረዳ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የልደት ካርድ ምዝገባ ቀን ላይ ማሻሻያ ሲያደርግ ከሥራ ሰዓት በተጨማሪ ቅዳሜ ከሰዓት ወረዳዎች አገልግሎት እንደሚሰጡ አስታውቋል፡፡ ከሥራ ሰዓት ውጪ አገልግሎት መስጠት ይጀመራል የተባለው ከሰኔ 22/2016 ጀምሮ ነው፡፡
በከተማው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጠው የልደት ካርድ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች በአስገዳጅነት የተቀመጠ ነው፡፡ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት ታች የሆኑ ሕፃናት የልደት ካርዱንምግኘት የሚችሉት በወላጆቻቸው በኩል የሚያገኙ ሲሆን፣ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎች ራሳቸው ተመዝግበው ካርዱን ማግኘት እንደሚችሉ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ መረጃ ያመለክታል፡፡
ለምዝገባ ሒደት መስፈርቶችን ያስቀመጠው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ከዘረዘራቸው ውስጥ የወላጆችን ማንነትን የሚገልፅ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ተጠቅሰዋል፡፡
በመዲናዋ ባሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ቅበላ የምዝገባ ቅድመ ሁኔታ የአሠራር ሥርዓት ሆኖ በአስገዳጅነት ከተቀመጠ ሁለት ዓመት ገደማ ተቆጥሯል። (ሚንበር ቲቪ)












