Homeዜናና ወቅታዊዜናአማል ማይክሮ ፋይናንስ ከዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በጋራ ለመሥራት ከሥምምነት...

አማል ማይክሮ ፋይናንስ ከዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በጋራ ለመሥራት ከሥምምነት ደረሱ

ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጠው አማል ማይክሮ ፋይናንስ እና ዳሸን ባንክ ባንክ ከወለድ ነጻ አገልግሎት (ሸሪክ) በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት አደረጉ፡፡ ከዳሸን ባንክ ጋር ስምምነት የፈጸመው አማል ማይክሮ ፋይናንስ፣ ለደንበኞች በሙራበሓ አሠራር ደንበኞቹን ፋይናንስ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

አማል ማይክሮ ፋይናንስ፤ ከዳሸን ባንክ ባንክ ከወለድ ነጻ አገልግሎት (ሸሪክ) ጋር በአንድነት ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ያደረጉት ባለፈው ሳምንት ሰኔ 15/2016 ነው፡፡

ስምምነቱ የፋይናንስ ተደራሽነትን መሠረት በማድረግ አማል ማይክሮ ፋይናንስ ከዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ አገልግሎት (ሸሪክ) የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ እና የልምድ ልውውጥ እንዲያገኝ የሚያስችለው መሆኑን የአማል ማይክሮ ፋይናንስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሞሲሳ ኢብሳ ለሚንበር ቲቪ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ የፋይናንስ ተቋማት፤ ያደረጉት ሥምምነት የአመል ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብራርተዋል፡፡

ከዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ አገልግሎት (ሸሪክ) ጋር ለመሥራት ሥምምነት የፈጸመው አማል ማይክሮ ፋይናንስ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጥ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ነው፡፡ በ34 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው የማይክሮ ፋይናንስ ተቋሙ፤ በአሁኑ ጊዜ በሸሪዓ መሠረት ሙራበሓ የተሰኘውን የትርፍ እና ኪሳራ መጋራት አሠራር አገልግሎት ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በመሥጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጧል፡፡

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋሙ እስካሁን ድረስ በሙራበሓ አገልግሎት ከስልሣ በላይ ግለሰቦች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሞሲሳ ኢብሳ ገልጸዋል፡፡

ከአመል ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ለመሥራት ሥምምነት የፈጸመው ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) በበኩሉ ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ያሉት ነው፡፡ የባንኩ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ተቀማጭ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጧል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular