Homeዜናና ወቅታዊዜናበአዲስ አበባ ያጋጠመው የነዳጅ እጥረት በመጪዎቹ ቀናት እንደሚፈታ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ያጋጠመው የነዳጅ እጥረት በመጪዎቹ ቀናት እንደሚፈታ ተገለጸ


በአዲስ አበባ ከተማ ከሰሞኑ ያጋጠመው የነዳጅ እጥረት በቀጣይ ቀናት ይፈታል ሲል የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት ገለጸ፡፡ በከተማዋ ባለፉት ቀናት የነዳጅ እጥረት ያጋጠመው በበዓል ቀናት ነዳጅ ከጅቡቲ አለመጫኑ ነው ተብሏል፡፡

የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው ነዳጅ እጥረት በቀጣይ ቀናት ሊስተካከል የሚችል ነው፡፡ የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እስመለዓለም ምሕረቱ ይህንኑ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡


ዋና ዳይሬክተሩ ነገሩኝ ብሎ ሪፖርተር ጋዜጣ እንዳስነበበው፣ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ ዋና ምክንያት ከአንድ ሳምንት በፊት በተከበረው የዒድ አል አድሓ በዓል ወቅት ነዳጅ ከጅቡቲ ስላልተጫነ ነው፡፡ አቶ እስመዓለም እንዳሉት በዓሉ በተከበረበት ሰኔ 9 እና ሰኔ 10/ 2016 ነዳጅ ከጂቡቲ አልተጫነም፡፡


በአዲ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ከሰሞኑ እየተስተዋለ ለሚገኘው የነዳጅ እጥረት ከበዓሉ ባሻገር አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ የመካሄደው የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ማደያዎች መፍረሳቸው መሆኑንም የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት ይገልጻል፡፡ እንደ ድርጅቱ መራ ከሆነ በኮሪደር ልማቱ የፈረሱት ስምንት ማደያዎች ፈርሰዋል፡፡ የፈረሱት ማደያዎች በሥራ ላይ የሚገኙ ማደያዎች ላይ ጫና እንደፈጠሩ ተገልጧል፡፡

በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች ከሰሞኑ ከሚታየው የነዳጅ እጥረት ባለፈ ማደያዎች ነዳጅን ከተጠቃሚዎች እንደሚደብቁ በተደጋጋሚ በአሽከርካሪዎች ቅሬታ የሚቀርብበበት ነው፡፡ የነዳጅና ኢነርጅ ባለሥልጣን በተለይ ሰው ሠራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲኖር በሚያደርጉ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ርምጃ እንደሚወስድ ሲገልጽ ቢቆይም፣ እስካሁን ድረስ ርምጃ አለመውሰዱ ይነገራል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular