Homeዜናና ወቅታዊዜናበጋዛ ጥቃት ቢያንስ 21 ሺሕ ሕፃናት ደብዛቸው መጥፋቱ ተገለጸ

በጋዛ ጥቃት ቢያንስ 21 ሺሕ ሕፃናት ደብዛቸው መጥፋቱ ተገለጸ

እስራኤል በጋዛ እየሰነዘረች በምትገኘው ጥቃት ቢያንስ 21 ሺሕ ሕፃናት የደረሱበት እንዳልታወቀ ሴቭ ዘ ችልድረን ገለጸ፡፡ ከጠፉት ሕፃናት ውስጥ አንዳንዶቹ እስራኤል ያወደመቻቸው ሕንጻዎች ፍርስራሽ ሳይወድቅባቸው አልቀረም ተብሏል፡፡

ሴቭ ዘ ችልድረን ይፋ ያደረገው አሐዝ፣ እስራኤል ከፈረንጆቹ ጥቅምር ወር የመጀመሪያ ቀናት አንስቶ የፈጸመችውን የሚያካትት መሆኑን አስታውቋል፡፡

የፍልስጤም ሕፃናት መብት ተቆርቋሪ የሆነው ቻይልድ ራይትስ ኦርጋናይዜሽን ችልድረን ኢንተርናሽናል ፓለስታይን ዋና ዳይሬክተር ካሊድ ኩዝማር፣ በጋዛ ሕፃናት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ነው ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ለአልጀዚራ ሲናገሩ፣ ድርጅታቸው ከ30 ዓመት በላይ በሥራ ላይ መቆየቱን አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት በጋዛ የሚሰነዘረው ጥቃት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንኳን ያልተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ካሊድ የእስራኤልን ጦርነት “በሕፃናት ላይ የሚፈጸም የጦር ወንጀል ነው” ብለውታል፡፡ በሕፃናት ላይ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ግፍ እየደረሰ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ጥቃቱ ሆን ተብሎ የሚፈጸም መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ከጠፉት 21 ሺሕ ሕፃናት ውስጥ አንዳንዶቹ ደብዛቸው የጠፋው በፍርስራሾች መሃል ተቀብረው ሊሆን የሚችል ግምት መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

እስራኤል በጋዛ ላይ የመጨረሻውን ጥቃት መሰንዘር ከጀመረች ወዲህ ደብዛቸው ከጠፉ ሕፃናት በተጨማሪ 9 ሺሕ 360 የዌስት ባንክ ነዋሪዎችን አስራለች፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል ሴቶች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡

እስራኤል በቅርብ ወራት እየፈጸመች በምትገኘው ጥቃት ቢያንስ 36 ሺሕ ንጹሐን ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular