Homeዜናና ወቅታዊዜናሁለተኛው የቲጃራ ቢዝፕረነር ኮንፍረንስ በዛሬው እለት ተካሔደ

ሁለተኛው የቲጃራ ቢዝፕረነር ኮንፍረንስ በዛሬው እለት ተካሔደ

ሁለተኛው የቲጃራ ቢዝፕረነር ኮንፍረንስ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሔደ። በኦሮሞ ባሕል ማዕከል የተካሔደው ኮንፍረንስ በኅትመትና ማሸጊያ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነበር።

ዛሬ እሑድ ሰኔ 16/2016 ለሁለተኛ ጊዜ በተካሔደው ኮንፍረንስ ላይ በኅትመትና ማሸጊያ ንግድ ዙርያ የልምድ ልውውጥ ተከናውኗል።

በመድረኩ ላይ ልምዳቸውን ካጋሩት ውስጥ የረዥም ዓመታት ልምድ ያላቸው ባለሞያዎች፣ የአንጋፋ ኅትመት ድርጅት መሥራቾች፣ መሪዎች እንዲሁም የኅትመት ማሽንና ዕቃ አቅራቢዎች ይገኙበታል።

በዛሬው ኮንፍረንስ ላይ ልምዳቸውን ካጋሩት ውስጥ በቅዱስ ቀርኣን የአማርኛ ትርጉም ኅትመት እንዲሁም በበርካታ እስላማዊ መጻሕፍት ኅትመት በቀዳሚነት የሚጠራው የነጃሺ ማተሚያ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓብደላ ሰዒድ ይጠቀሳሉ።

በኮንፍረንስ ላይ የኅትመት እና ማሸጊያ ዘርፍ ቴክኖሎጂዎች፣ የሥራ ዕድሎች፣ ፈተናዎችን ጨምሮ በዘርፉ ስኬታማ መሆን የሚቻልበት መንገድ ላይ ተጋባዥ እንግዶች ተመክሯቸውን አጋርተዋል።

በዚህ የተመክሮ መጋራት ወቅት በዋነኝነት ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች የኅትመትና ማሸጊያ ንግድ ዘርፍን በአነስተኛ ካፒታል እንዴት መቀላቀል እንደሚችሉ ከተጋባዥ እንግዶቹ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የቲጃራ ቢዝፕረነር የመጀመሪያውን ኮንፍረንስ ያካሄደው በሚያዝያ ወር መጨረሻ ላይ ነበር። በወቅቱ ኮንፍረንስ ላይ በጂጂታል አማራጮች ላይ በሚገኙ ሥራዎች ዙርያ ገለፃ ተሰጥቷል።

ቲጃራ ቢዝፕረነር በንግድ እና ሥራ ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ በሚሠራው “ቲጃራ ጆርናል” የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሥር የታቀፈ ነው። በዛውያ ቲቪ የሚቀርበው ቲጃራ ጆርናል የቴሌቪዥን ፕሮግራም፣ የሚቀርበው በጋዜጠኛ ሙሣ ኑረዲን መሆኑ ይታወቃል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular