ሰኞ , محرم 9, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናየንጉሥ አባ ጂፋርን የሑጃጅ ሕንጻ ለቀጣዩ ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ወደ ሥራ...

የንጉሥ አባ ጂፋርን የሑጃጅ ሕንጻ ለቀጣዩ ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ወደ ሥራ ለመመለስ ጥረት እንደሚደረግ ተገለፀ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ሳዑዲ ዐረቢያ መካ ከተማ ውስጥ የሚገኝውን የንጉሥ አባ ጂፋር የኢትዮጵያውያን እንግዳ ማረፊያ ሕንጻ ችግር ለመፍታት እንደሚሠራ ያስታወቀው በፕሬዝዳንቱ በኩል ነው። የእንግዳ ማረፊያው በዘንድሮው ዓመት የብቃት ደረጃ ባለማሟላቱ አገልግሎት ሳይሰጥ መቅረቱ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ትናንት ቅዳሜ ሰኔ 15/2016 ምሽት ባወጣው መረጃ፣ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚገኙት ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የመሩት ቡድን ለበርካታ ዓመታት ለኢትዮጵያውያን ሑጃጅ ማረፊያነት ሲያገለግል የቆየውን ሕንጻ ጎብኝቷል።

በንጉሥ አባ ጂፋር የተገነባውና ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ሕንጻ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ወቅት አገልግሎት አለመስጠቱን መጅሊስ አረጋግጧል። እንደ ምክር ቤቱ ከሆነ፣ ሕንጻው ለኢትዮጵያውያን አገልግሎት ያልሰጠው በሳዑዲ ዐረቢያ መንግሥት የተቀመጠውን የብቃት ደረጃ ሳያሟላ በመቅረቱ ነው።

ንጉሥ አባ ጂፋር

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ከመሩት ልዑክ ጋር ሕንጻውን ከጎበኙ በኋላ የሑጃጅ ማረፊያው ታሪካዊ አሻራውን በሚያጎለብት መልኩ፣ መሟላት ያለበትን በማስተካከል በሚቀጥለው ዓመት ችግሩ ተፈትቶ ለእንግዶች ማረፊያነት የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ እንዲቀጥል መደረግ እንደሚኖርበት ተናግረዋል ተብሏል።

የንጉሥ አባ ጂፋር የኢትዮጵያውያን ሑጃጅ ማረፊያ የተገነባው በ1900 እንደሆነ ይነገራል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments