Homeዜናና ወቅታዊዜናየዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በነገ ዕለት ሊሰጥ ነው

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በነገ ዕለት ሊሰጥ ነው



በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠው የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊሰጥ ነው፡፡ ነገ ዐርብ ሰኔ 14/2016 በሚሰጠው ፈተና ተማሪዎች በሦስት ክፍለ ጊዜ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል፡፡

እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ ከሆነ የነገው የጊዜ ሠሌዳ ለፈተና በድጋሚ የሚቀመጡ ተፈታኞችን የሚያካትት እንደሚሆን ተገልጧል፡፡ በነገው ዕለት ፈተናውን ለመውሰድ የአገልግሎት ክፍያ  የከፈሉና የሥም ዝርዝራቸው ከቀድሞው ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች ይሆናሉ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተመራቂዎች አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎችን በተመለከተ በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

ባሳለፍነው ዓመት በሐምሌ ወር መሰጠት የተጀመረው የመውጫ ፈተና ለሁለተኛ ጊዜ በያዝነው ዓመት የካቲት ወር ላይ ተሰጥቶ ነበር።


ከዚህ ቀደም በየካቲት ወር ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጠው ፈተና በ47 የመንግሥት ተቋማት እና በ84 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን በመንግሥት እና በግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149 ሺሕ 145  ተፈታኞች  በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደተፈተኑ ይታወሳል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular