Homeዜናና ወቅታዊዜናየንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ

የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሔደው ስብሰባ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ አደረገ። ምክር ቤቱ በስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ዐርብ ሰኔ 7/2016 ባካሔደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል በንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ይገኝበታል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የንብረት ታክስ በከተሞች ነዋሪ በሆነው ሕዝብ መካከል ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ለማስፈን፤ የመንግሥት አገልግሎቶችን በተሻለ ጥራትና በዘመናዊ ዘዴ ማቅረብ ለማስቻል እና የከተማ መሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን በቀጣይነት ለመተግበር የሚወጣውን የኢንቨስትመንት ወጪ በንብረት ዋጋ ማደግ ምክንያት በሚጣል ታክስ አማካኝነት ለመሰብሰብ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሷል።

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ተፈጻሚነት ይኖረዋል የተባለው አዋጁ፣ ክልሎችም ከተጨባጭ ሁኔታቸው ጋር በተጣጣመ መልኩ የየራሳቸውን የንብረት ታክስ ሕግ እንዲያወጡ የሚያስችላቸው መሆኑም ተገልጿል። ረቂቅ አዋጁ ይህን ለማስፈጸም የሚረዳ ነው ተብሏል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ገልጿል።

ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሪፎርም እና የካፒታል ማሳደጊያ ዕቅድ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ጋር የሁለተኛ ዙር የከተሞች የውሃ መጠጥ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ ብድር ለማግኘት የተፈረመውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ ይገኝበታል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular