Homeዜናና ወቅታዊዜናለሑጃጆች የተዘጋጀው የአየር ታክሲ የመጀመሪያውን በረራ አከናወነ

ለሑጃጆች የተዘጋጀው የአየር ታክሲ የመጀመሪያውን በረራ አከናወነ

ሳዑዲ ዐረቢያ በተያዘው ዓመት ለሑጃጆች በአማራጭነት ያቀረበችው የአየር ታክሲ የመጀመሪያውን በረራ በዛሬው እለት አከናወነ፡፡ በራሪ ታክሲዎቹ ለሑጃጆች ከመዲና ወደ መካ ከሚሰጡት የትራንስፖርት አገልግሎት በተጨማሪ የሕክምና ቁሳቁሶችን ያጓጉዛሉ ተብሏል፡፡

ዛሬ ረቡዕ የአየር ታክሲው የመጀመሪያውን በረራ ሲያከናውን የሳዑዲ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፈዎች ተገኝተዋል፡፡ ባለሥልጣናቱ በራሪ ታክሲዎቹ በዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ከዚህ ቀደም አስታውቀው ነበር፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ በይፋ ሥራ ያስጀመረችው በራሪ ታክሲ፣ ከንጉሥ ዐብዱልዓዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ የተቀበሏቸውን ምእመናን ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ ሆቴሎች በአየር አንሳፈው ያደርሳሉ፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ በዚህ ዓመት ለሐጅ ተጓዦች ያቀረበችው በራሪ ታክሲ ከአራት እስከ ስድስት ሰው የሚያሳፍር ነው፡፡

ከግንቦት 1/2016 አንስቶ ሑጃጆችን እየተቀበለች የምትገኘው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ እስከ ትናንት ማክሰኞ ሰኔ 4/2016 ድረስ 1.5 ሚሊዮን ምዕመናንን ከመላው ዓለም ተቀብላለች፡፡ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ምዕመናን በሐጅ ሥነ ሥርዓት ክንውን ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ይፋ ባደረጉት መረጃ መሠረት፣ 1 ሚሊዮን 483 ሺሕ 312 ምዕመናን በአየር ተሳፍረው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ደርሰዋል፡፡ 59 ሺሕ 273 ምዕመናን በየብስ የገቡ ሲሆን፣ 4 ሺሕ 710 ምዕመናን ባሕር አቋርጠው ሳዑዲ ዐረቢያ ተገኝተዋል፡፡

የ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ከጁመዓ ዙል ሒጃ 8 አንስቶ ለተከታታ ቀናት ይከናወናል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular