Homeዜናና ወቅታዊዜናበዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሐጅ ዕድል ተሰጠ

በዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሐጅ ዕድል ተሰጠ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሐጅ ዕድል ሰጠ። የሐጅ ሥነ ሥርዐት ለመከወን የሚያስችለውን ቪዛ ያገኙት ዓብዱልወሐብ ኢብራሂም እና ሙሐመድ ማሕሙድ የተባሉ ወጣቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 24/2016 በጽሕፈት ቤቱ ባከናወነው ሥነ ሥርዐት ላይ ለወጣቶቹ ሥጦታውን ማበርከቱን ይፋ አድርጓል። ሁለቱ ወጣቶች የሐጅ ሥነ ሥርዐት ለመከወን የሚያስችለውን የቪዛ ማግኘታቸውን ይፋ ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ናቸው።

ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ተሳትፈው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡበት ውድድር የተካሄደው በሊቢያ ሀገር ነው።

ከ60 በላይ ሀገራት ተሳትፈውበታል በተባለው ውድድር ላይ ዐብዱልወሐብ ኢብራሂም በቂርኣተል አሸር አንደኛ ደረጃ በመያዝ ሲያጠናቅቅ፣ ሙሐመድ ማሕሙድ በሠላሳ ጁዝ ሁለተኛ ደረጃ ማስመዝገቡ ተገልጿል።

ወጣቶቹ ዐብዱልወሐብ እና ሙሐመድ የቁርኣን ጥናት ሲያከናውኑ የቆዩት በዘይድ ኢብን ሳቢት የቁርአን ማኅበር ውስጥ መሆኑ ታውቋል።

በዛሬው የሽልማት ሥነ ሥርዐት ላይ የቁርኣን ጥናት ማኅበሩ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶታል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular