Homeዜናና ወቅታዊዜናበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ፈተና የቀን ለውጥ እንዲደረግበት ተጠየቀ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ፈተና የቀን ለውጥ እንዲደረግበት ተጠየቀ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ፈተና የቀን ለውጥ እንዲደረግበት የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡ ምክር ቤቱ በበዓል ማግሥት የሚሰጠው ፈተና በተማሪዎች ውጤት ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጧል፡፡  

የክልሉ እስልምና ጉዳዮ ከፍተኛ ምክር ቤት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ግንቦት 21/2016 በጻፈው ደብዳቤ፣ ፈተናው ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚከበረው የዒድ አል አድሓ በዓል እለት እንደሚሰጥ በመጥቀስ፣ የቀን ለውጥ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ የፈተናው ቀን ከበዓሉ ጋር በአንድነት መሰጠቱን በሕገ መንግስሥቱ የተቀመጠውን የሃይማኖትን እኩልነት የሚጥስ ነው ብሎታል፡፡ ምክር ቤቱ በተጨማሪም የበዓል ዋዜማ እና ማግሥት ላይ የሚደረግ ፈተና በተማሪዎች ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረውም ነው የገለጸው፡፡

የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ክፍተኛ ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ዞኖች ትምህርት መምሪያዎች፣ ወረዳ እና ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች የፕሮግራም ለውጥ ያድርጉ ብሏል፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ስምንተኛ ክፍል ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረውን ክልል አቀፍ ፈተና ለስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች መስጠት የጀመረው ከባለፈው ዓመት አንስቶ ነበር፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular