እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናፊሊፒንስ የሐላል ቱሪዝም ገበያውን ልትቀላቀል መሆኑን አስታወቀች

ፊሊፒንስ የሐላል ቱሪዝም ገበያውን ልትቀላቀል መሆኑን አስታወቀች

የደቡብ ምሥራቅ እስያዋ ሀገር ፊሊፒንስ፣ በሀገሯ በሚገኝ ትልቁ የባህር ዳርቻ ውስጥ የሐላል ቱሪዝም አማራጮችን ለማቅረብ እየሠራች እንደምትገኝ አስታወቀች፡፡ ሀገሪቱ የሐላል ቱሪዝም አማራጮችን ለማስጀመር ዕቅድ የያዘችው በትልቁ የባህር ዳርቻዋ ስር በሚገኘው ቦራኬይ ሪዞርት ውስጥ መሆኑን ይፋ አድርጋለች፡፡

ፈሊፒንስ የሐላል ቱሪዝም የምታስጀምርበት ቦራኬይ ሪዞርት የሚገኝት የባህር ዳርቻ ሥመ ገናና ከሆኑ የዓለማችን የቱሪዝም መዳረሻዎች ውስጥ አንደኛው ነው፡፡

25 በመቶ የቱሪዝም ገቢዋን ባህር ዳርቻዎቿን ከሚጎበኙ ቱሪስቶች የምታገኘው ፈሊፒንስ፣ በቀጣይ ሙስሊም ጎብኚዎችን በይበልጥ ለመሳብ እየተንቀሳቀሰች መሆኑንም ገልጻለች፡፡ የሀገሪቱ ቱሪዝም መስሪያ ቤት ባለሥልጣን የሆኑት ክሪስቲና ፈራስኮም ይህንኑ የፊሊፒንስን ዕቅድ ለመገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል፡፡ ፍራስኮ በቦራኬይ ሪዞርት በቅርቡ የሐላል ቱሪዝም አማራጮችን ለማስጀመር በመስሪያ ቤታቸው እና በሪዞርቱ መካከል ውይይት እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

የሐላል ቱሪዝም ለማስጀመር እየሠራች መሆኑን ያሳወቀችው ፊሊፒንስ፣ ካላት 12 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ የሙስሊም ዜጎች ቁጥር 10 በመቶ ነው፡፡ ሀገሪቱ እ.አ.አ የ2024 አዲስ ዓመት ከገባ ወዲህ ባሉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ 2 ሚሊዮን ጎብኚዎችን አስተናግዳለች፡፡ ፊሊፒንስ ከጎብኚዎቿ መካከል ከሙስሊም ሀገራት የሚነሱት 10 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸውን ገልጻለች፡፡

የሐላል ቱሪዝም አቅርቦት በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኘው ሐላል ኢንዱስትሪ አንደኛው ዘርፍ ነው፡፡ ሰባት ዘርፎችን የሚያቅፈው ይህ ኢንዱስትሪ፤ በሥሩ ምግብን ጨምሮ እስላማዊ ፋይናንስ፣ ሐላል ምግብ፣ ሐላል ፋሽን፣ ሐላል ሚዲያ እና መዝናኛ፣ የመድኃኒት እና ሐላል መዋቢያዎችን ያካትታል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments