እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናሳዑዲ ዐረቢያ ለአንድ ሺሕ ፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦች የሐጅ ዕድል ሰጠች

ሳዑዲ ዐረቢያ ለአንድ ሺሕ ፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦች የሐጅ ዕድል ሰጠች

ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ከመላው ዓለም ምዕመናንን እየተቀበለች የምትገኘው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ለአንድ ሺሕ ፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦች የሐጅ ዕድል መስጠቷን አስታወቀች፡፡ በዚህ ዕድል ከሰማዕታት በተጨማሪ በእስራኤል ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን ቤተሰቦች ተካተዋል፡፡

ሀገሪቱ ለፍልስጤማዊያን ሰማዕታት እና የግፍ እስረኛ ቤተሰቦች በሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ እንዲሳተፉ ዕድል መስጠቷን ያስታወቀችው፣ በንጉሥ ሰልማን ቢን ዓብዱልዓዚዝ አማካይነት መሆኑን የሀገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡ ሀገሪቱ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ለአንድ ሺሕ ፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦች የሐጅ ዕድል ሰጥታ ነበር፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ ከፍልስጤማዊያን ውጪ ከመላው ዓለም ከ88 ሀገራት የተውጣጡ 1300 ምዕመናን የሐጅ ዕድሉን ሰጥታለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የተካተቱት 22 ምዕመናን በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ ሕክምና አግኝተው እንዲነጣጠሉ የተደረጉ መንትያ ሕፃናት ቤተሰቦች ናቸው፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ በዘንድሮው 1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከመላው ዓለም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን ትቀበላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሳዑዲ ዐረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሑጃጆችን መቀበል ከጀመሩበት ግንቦት 1/2016 አንስቶ ለሐጅ ወደ ሀገራቸው የገባው የምዕመናን ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መድረሱን ይፋ አድርገዋል፡፡

የሳዑዲ ዐረቢያ የፓስፖርት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክቶሬት እንዳስታወቀው፣ ይፋ የተደረገው የምዕመናን ቁጥር በሁሉም የመጓጓዣ አማራጮች የገቡትን ነው፡፡ በዳይሬክቶሬቱ መረጃ መሠረት ከምዕመኑ መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የገቡት በአውሮፕላን ነው። የእነዚህ ምዕመናን ቁጥር 523 ሺሕ 729 ነው።

በድንበር ተሻግረው የገቡ 9 ሺሕ 210 ምዕመናን እንዳሉ የገለጸው ዳይሬክቶሬቱ፣ 19 ምዕመናን በባህር ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ደርሰዋል ብሏል። የሀገሪቱ ባለሥልጣናት 19ኙ ምዕመናን የተነሱት ከየት እንደሆነ የጠቀሱት ነገር የለም። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments