እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናአልጄሪያ እስራኤል በራፋህ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ልታቀርብ ነው

አልጄሪያ እስራኤል በራፋህ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ልታቀርብ ነው

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር አልጄሪያ፤ እስራኤል በራፋህ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድርጅት ልታቀርብ መሆኑን አስታወቀች፡፡ የሀገሪቱ የውሳኔ ሐሳብ የመጣው፣ እስራኤል አዲስ ጥቃት በመሰንዘር ንጹሐን ላይ ግድያ ከፈጸመች በኋላ ነው፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአልጄሪያ ቋሚ ተጠሪ የሆኑት አምባሳደር አማር ቤንጃማ ትናንት ማክሰኞ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ሀገራቸው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምታቀርበው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ አጭር እና ዋናው ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ከፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ የተናገሩት አምባሳደሩ፣ የአልጄሪያ ጥያቄ እስራኤል በራፋህ ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት እንድታቆም ነው፡፡ አምባሳደር አማር ቤንጃማ የተሳተፉበት ስብሰባ የተጠራው በራሷ በአልጄሪያ ነበር፡፡

አልጄሪያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ፣ በተለያዩ ሀገራት ድጋፍ ያገኘ ነው፡፡ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቡን በተመለከተ የተናገሩት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፈረንሳይ ቋሚ ተጠሪ ኒኮላ ደ ሪቬራ፣ በራፋህ ያለው ሁኔታ የሕይወት እና ሞት ጉዳይ ስለሆነ አስቸኳይ ርምጃ መውሰድ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆነ አሳስበዋል፡፡

እስራኤል ባለፈው እሑድ በራፋህ በተደጋጋሚ ጥቃት የሰነዘረችው በተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ላይ ነው፡፡ እስራኤል ትናንት ማክሰኞ በሰነዘረችው የመጨረሻ ጥቃት ቢያንስ 21 ንጹሐን ተገድለዋል፡፡

እስራኤል ከሁለት ቀን በፊት በፈጸመችው ተመሳሳይ ጥቃትም ከንጹሐን በተጨማሪ በራፋህ ውስጥ የሚገኘው የኩዌት ስፔሻሊቲ ሆስፒታል ሁለት የሕክምና ባለሞያዎችን ገድላለች፡፡ ይህንኑ ጥቃት ተከትሎም ሆስፒታሉ ተዘግቷል፡፡ ሆስፒታሉ እሑድ ምሽት እስራኤል በሰነዘረችው ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው 249 ሰዎች ሕክምና ሲሰጥ የነበረ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments