እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናከግማሽ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ገብተዋል ተባለ

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ገብተዋል ተባለ

የሳዑዲ ዐረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት ለሐጅ ወደ ሀገራቸውን የገባውን የምዕመናን ቁጥር ይፋ አደረጉ። ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት ሳዑዲ ዐረቢያ የደረሱ ምዕመናን ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን ተሻግሯል።

የሳዑዲ ዐረቢያ የፓስፖርት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክቶሬት እንዳስታወቀው፣ ይፋ የተደረገው የምዕመናን ቁጥር በሁሉም የመጓጓዣ አማራጮች የገቡትን ነው።

በዳይሬክቶሬቱ መረጃ መሠረት ከምዕመኑ መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የገቡት በአውሮፕላን ነው። የእነዚህ ምዕመናን ቁጥር 523 ሺሕ 729 ነው።

በድንበር ተሻግረው የገቡ 9 ሺሕ 210 ምዕመናን እንዳሉ የገለጸው ዳይሬክቶሬቱ፣ 19 ምዕመናን በባህር ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ደርሰዋል ብሏል። የሀገሪቱ ባለሥልጣናት 19ኙ ምዕመናን የተነሱት ከየት እንደሆነ የጠቀሱት ነገር የለም።

ሳዑዲ ዐረቢያ ለዘንድሮ 1445ኛ ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ከግንቦት 1/2016 አንስቶ ከመላው ዓለም ምዕመናንን እየተቀበለች እንደምትገኝ ይታወቃል። ሀገሪቱ ባለፈው ዓመት ለሐጅ የተቀበለቻቸው ምዕመናን ቁጥር ከ1 ሚሊዮን 800 ሺሕ በላይ ነው።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments